ሕዳር 23 ቀን 2013 

ጀግናዋ ም/አስር አለቃ ከሀዲውን ኮሎኔል ማንቁርቱን ይዛ አስረከበች ።

20ኛ ቃሉ ክ/ጦር ሰሜን ዕዝ ካሏት የጦር ክፍሎች ውስጥ አንዱ ነው። በዚህ ክ/ጦር 1ኛ ብርጌድ 1ኛ ሻለቃ አባል የሆነችው ምክትል አስር አለቃ ገባያነሽ ደባልቄ የሻለቃው አዛዥ ኮሎኔል ሰለሞን ገ/ዮሃንስ አጃቢ ነች ። ጁንታ መሆኑን ግን አታውቅም ።

One of Brave Ethiopian Soldiers 2020

የእብሪት ርምጃቸው ከመጀመሩ ከ3 ቀናት በፊት ሰራዊቱ የምግብና መጠጥ አገልግሎት የሚያገኝባቸውን መንገድ በመዝጋት ሰራዊቱን ለከፍተኛ ርሃብና ጥም ዳርጏል ።

ሁሉም የሰራዊት አባል የግል ትጥቁን በአንድ ክፍል በማስቀመጥ በህብረተሰብ የድጋፍ ስራዎች ላይ እንዲረባረብ ማድረጉን ትናገራለች ።

በተለይም ጥቅምት 24 ቀን 2013 ምሽት ላይ ሁሉንም የጥበቃ ቦታዎች በትግራይ ተወላጅ የሰራዊት አባላት እንዲሸፈኑ በማድረግ ፣ የከሃዲው ቡድን ልዩ ሃይልና ሚሊሻ ምንም አይነት ዝግጅትና ትጥቅ ባልነበረው ሰራዊታችን ላይ ከፍተኛ ተኩስ እንዲከፍትም አድርጏል ብላለች ።

ሆኖም ታላቅ ጀግንነትና ኢትዮጵያዊ ማንነትን የወረሰው ጀግናው ሃይላችን የማይታሰቡ ጀብዶችን ጭምር በመፈፀም ወደ ኤርትራ በመሸሽ ራሱን ማዳን ችሏል ብላለች ።

በዚህ ሁሉ ግፍና በደል መሃል የሻለቃዋ ዋና አዛዥና ለዘመናት የመራቸውን የሃገር መከላከያ ሰራዊት አባላት ይካደው ኮሎኔል ሰለሞን ገ/ዮሃንስ ራሱን መፀዳጃ ቤት ውስጥ በመደበቅ በጁንታው የተሰጠውን ተልዕኮ መፈፀም እንደጀመረ በሃዘን ስሜት ውስጥ ሆና አስታውሳለች ።

ውትድርና በኢትዮጵያዊነት ፍቅር መታጠብና በጀግንነት ካባ መድመቅ ነው የምትለው እንስቷ ጀግና ፣ ራስህን ለሃገር አሳልፈህ ከሰጠህ ኢትዮጵያዊ መሆን ብቻውን ጀግንነትን ይወልዳል ስትል የቀድሞ አለቃዋን እንዴት ከስሯ እንዲንበረከክ እንዳደረገችሁ እንዲህ ታጫውተናለች ።

“… ሰራዊታችን በታፈነበት ጥቅምት 24 ምሽት 2 ሰዓት ላይ በከባድ መሳሪያ የታጀበ ተኩስ ወደ ካምፓችን ተተኮሰ፣ በዚህ ሰዓት ወደመፀዳጃ ቤት ራሱን የደበቀው ካሃዲው አዛዥ ተብየ እኔ በትግራይ ሚሊሻና ልዩ ሃይል ጥይት ከምሞት አንተን ገድየ ራሴን አጠፋለሁ አልኩት፣ ተኩሱ በርትቷል፣ ሁሉም ራሱን ለማዳን ወደህሊናው የመጣለትን አማራጭ እየተጠቀመ ይሯሯጣል…”

“… በመጨረሻም ከተደበቀበት መፀዳጃ ቤት እንዲወጣና እኔ የምለውን ብቻ እንዲፈፅም እሽ የማይል ከሆነ ግን እንደምገድለው አስጠነቀቁት፥ እሱም በፍርሃት ውስጥ ሆኖ ከተደበቀበት ቦታ ወጥቶ ወደነገርኩት ቦታ መጣ፥ ሽጉጡንና ማዕረጉን እንዲሰጠኝ አደረኩ፣ ከዛም ጫማውን እንዲያወልቅ አድርጌ በየመንገዱ ከማገኛቸው የሰራዊት አባላት ጋር በመተባበርና ሙሉ ለሊት የእግር ጉዞ በማድረግ ኤርትራ ይዤው በመግባት ታማኝ እና ሙሉ ኢትዮጵያዊ ለሆኑ አመራሮች አስረከብኩ  ።”

ሰራዊታችን በራሱ ወገኖች የደረሰበትን በቃላት የማይገለፅ ግፍና በደል ተሸክሞ ቂምን ሳይሆን ኢትዮጵያዊ ፍቅር አስቀድሞ ለድል በመብቃቱ ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማትም ምክትል አስር አለቃ ገበያነሽ ደባልቄ ስሜቷን አጋርታናለች ።

ኢትዮጵያችን ምንም እንኳን በራሱ ጉያ ተወሽቀው ሳቋን እየቀሙ ውርደቷን የሚያፋጥኑና መበተኗን ገሃድ ለማውጣት ሌት ተቀን የሚሯሯጡ ወጪት ሰባሪዎች ቅዠታቸውን ቢኖሩትም ክብሯን የሚያስጠብቁ ከራሳቸው ህይወት ይልቅ የሃገራችውን ክብር የሚያስቀድሙ፣ የማይታመን ጀግንነት እየፈፀሙ ኢትዮጵያችን ከፍ ያደረጉ የበርካታ የቁርጥ ቀን ልጆች ባለቤት ናት ኢትዮጵያ !

ምክትል አስር አለቃ ገባያነሽ ደባልቄም ጀግና ማፍራት የማትሰለቸው ሃገራችን ከሰጠችን እንቁ ኢትዮጵያውያን አንዷ ናት፥ እንዳንች አይነት ኩሩ ኢትዮጵያዊ ሁሌም በኢትዮጵያዊ ክብር ደምቆ ይኖራል ።

የከሃዲዎች መጨረሻ ሃገርን ለማዋረድ ባሴሩት ህልም ውስጥ ተጠልፎ መውደቅ ነው ።

By Eyasu Esayas

Entrepreneur, Writer, Business advocate and Teacher. Nice to have every soul on board. Eyasu do adore the HUMAN Nature. Join the Wonderful Team.

How is that?

Discover more from Essu Center

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading