ጽንፈኛው የሕወሃት ቡድን በመከላከያ ሰራዊት ላይ የፈጸመውን ጥቃት የሚያወግዝ ሰላማዊ ሰልፍ በኦሮሚያ ከነገ ህዳር 3/2013 ጀምሮ ሊደረግ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የሕወሃት ጁንታ በሰሜን ዕዝ ጀግኖች የመከላከያ ሰራዊት አባላት ላይ ለመስማት እንኳን የሚከብድ ዘግናኝ የሆነ ሰይጣናዊ ጭፍጨፋ መፈጸሙ የኦሮሚያ ክልል ህዝብን እንዳስቆጣ ተገልጿል፡፡

ይህ አሳፋሪ ተግባር በዓለም ታሪክ ከተፈጸሙ እጅግ አሳፋሪ የጦር ወንጀል ታሪኮች ውስጥ ተመዝግቦ ይኖራልም ተብሏል፡፡

በመላው የኦሮሚያ ዞኖች፣ ከተሞች እና ወረዳዎችም ሰላማዊ ሰልፎች ለማድረግ በርካታ ጥያቄዎች በመቅረብ ላይ እንደሚገኙ በምክትል ፕሬዝዳንት ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ አቶ አዲሱ አረጋ ገልጸዋል፡፡

ሰላማዊ ሰልፎቹ ከነገ ህዳር 03/2013 ጀምሮ ታላላቅ ሰላማዊ ሰልፎች እንዲደረጉ መፈቀዱን አቶ አዲሱ ገልጸዋል፡፡

የሰላማዊ ሰልፎቹ ዓላማ ህገ ወጡ የሕወሃት ጁንታ ከግብረ አበሩ ኦነግ ሸኔ ጋር በመቀናጀት በጀግናው የሰሜን ዕዝ ሰራዊት አባላት ላይ የፈጸመውን ዘግናኝ ጭፍጨፋ እና የጦር ወንጀል በማውገዝ ጥፋተኞች ለህግ እንዲቀርቡ መጠየቅ፣ መንግስት ሕግን ለማስከበር እየወሰደ ያለውን እርምጃ በመደገፍ ለጀግናው የመከላከያ ሰራዊት እስከ ህይወት መስዋዕትነት ድረስ አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ያላቸውን ዝግጁነት ለመግለጽ፣ የአጥፊው ጁንታ ጥፋት የጥቂት ስግብጎቦች ሴራ እንጂ የሰላም ወዳዱን የየትኛውንም ህዝብ ፍላጎት የማይወክል መሆኑን እና በጁንታው በተፈጸመው ዘግናኝ ጥፋት ምክንያት የኢትዮጵያ አንድነት የማይፈርስ፣ የህዝቦች ወንድማማችነት እንደማይናጋና የጁንታውን ሀገር የማፍረስ ሴራ በቁርጠኝነት ለመታገል ያላቸውን አቋም ለመግለጽ ነው ተብሏል፡፡

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የጸጥታ አካላትም የህዝቡን የሰላማዊ ሰልፍ ጥያቄ ለማስተናገድ በቂ ዝግጅት ማድረጋቸው ተገልጿል፡፡

ሰላማዊ ሰልፈኞቹም ከጸጥታ ኃይሎች ጋር በመተባበር ሰልፎቹ በሰላም እንዲጠናቀቁ የሚጠበቅባቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ፣ እራሳቸውንም ከኮቪድ- 19 ስርጭት ለመከላከል አስፈላጊዉን ጥንቃቄ በማድረግ እንዲንቀሳቀሱ አቶ አዲሱ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

By Eyasu Esayas

Entrepreneur, Writer, Business advocate and Teacher. Nice to have every soul on board. Eyasu do adore the HUMAN Nature. Join the Wonderful Team.

How is that?

Discover more from Essu Center

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading