ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በቁርጠኝነት ለጀመርነው ኦፐሬሽን ውጤታማነት ህዝባችን ከመከላከያ ሃይላችን ጎን በመቆም ታሪካዊ ደጀንነቱን በተግባር እንዲያረጋግጥ እንዲሁም ትውልድ እና ሃገር በማዳን ተልእኮ ላይ በንቃት እንዲረባረብ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ 

ም/ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ገፃቸው ባስተላለፉት መልእክት ላለፉት ዓመታት በህውሃት ቡድን ቅጥያጣ ጥፋት እና ድፍረት “ትዕግስታችን” እንደፍርሃት እንዲሁም “አስተዋይነታችን” እንደድክመት እየተቆጠረ ህዝብና መንግስት ከልክ ያለፈ ዋጋ እንዲከፍሉ ማስገደዱ አስታውሰዋል፡፡ 

ከሁሉ በላይ በዚህ ኢትዮጵያ-ጠሉ ከሃዲ ቡድን ከቀናት በፊት የሀገር ሉዓላዊነት መገለጫ በሆነው የመከላከያ ኃይል ላይ ጥቃት ፈፅሟል፡፡ 

በዚህ ደርዝ ባጣ ድፍረቱ የአማራን ህዝብ ለመውረር በጠገዴ ቅራቅርና ሶሮቃ አካባቢ ያካሄደው ተደጋጋሚ ጥቃት እንዲሁም እስከጎንደር ለመዝለቅ ያሳየው ንቀት፣ እብሪት እና ድፍረት እጅግ አሳፋሪ መሆኑ ልብ ይሏል፡፡

ይሁንና! የከሃዲውን ቡድን ረጅም ህልም በአጭሩ የቀጩት የመከላከያ ሃይል፤ የአማራ ክልል ልዩ ሃይል እና ሚሊሻዎች ፈጣን የአጸፋ ምላሽ በመውሰድ ያስመዘገቡት ውጤት በእጅጉ የሚደነቅ እና የሚያስመሰግን ነው፡፡ 

በከሃዲ ቡድኑ ሴራ ለዘመናት ሰምና ወርቅ ሆኖ የኖረው የአማራ እና የትግራይ ህዝብ ግንኙነት በዋዛ የሚበጠስ ሳይሆን፤ ታሪካዊ አንድነታቸው እና የተጋመደው ህብረታቸው እየጠበቀ ወደ ላቀ ደረጃ የሚሸጋገር ይሆናል፡፡ 

ረጅም ጊዜ የቆየውን የሃገራችን መዋቅራዊ ችግር በማያዳግም አግባብ ለመፍታት ይህ ከሃዲ ቡድን መወገድ ይኖርበታል፡፡ በተለያየ አቅጣጫ የቡድኑ መናጆዎችም በየአካባቢው ተጨማሪ ጥቃት እንዳይሰነዝሩ በፍጥነት መነቀል ይኖርባቸዋል፡፡ 

የመከላከያ ኃይላችን የጀመረው ኦፐሬሽን ፍጥነትና ጥንቃቄን በሚዛን አስቀምጦ የሚጓዝ ነው፡፡ ፍጥነቱ ከሃዲውን ቡድን በአጭር ጊዜ ለፍርድ ለማቅረብ ሲሆን፤ ጥንቃቄው ደግሞ ሰፊውን የትግራይ ህዝብ ከጉዳት ለመጠበቅ ያለመ ነው፡፡ 

በአሁን ጊዜ የመከላከያ ሃይላችን በተለያዩ ግንባሮች ግዳጁን በብቃት እየተወጣ ሲሆን፤ ደረጃ በደረጃ አኩሪ ገድል ማስመዝገቡን ቀጥሏል፡፡

By Eyasu Esayas

Entrepreneur, Writer, Business advocate and Teacher. Nice to have every soul on board. Eyasu do adore the HUMAN Nature. Join the Wonderful Team.

How is that?

Discover more from Essu Center

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading