የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ራሱን ችሎ ሊቀ ጳጳስ ተመድቦለት እንዲመራ ቅዱስ ሲኖዶስ ወሰነ።

በህገ ቤተክርስቲያኑ የሚገኘው አንቀፅ 50 በአሁኑ ጊዜ ለሀገረ ስብከቱ አሰራር የማይመች ሆኖ ስለተገኘ ከህገ ቤተክርስቲያኑ እንዲወጣ ሲኖዶሱ መወሰኑም ተገልጿል።

ከጥቅምት 11 ጀምሮ ለ13 ቀናት ሲያካሄድ የቆየውን ዓመታዊ መደበኛ ስብሰባ በማጠናቀቅ ማህበራዊ እና መንፈሳዊ ውሳኔዎች ማሳለፉን ቅዱስ ሲኖዶሱ አስታውቋል።

የቅዱስ ሲኖዶሱ ዋና ፀሐፊ ብፁእ አቡነ ዮሴፍ የጉባኤውን መጠናቀቅ አስመልክተው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የቤተክርስቲያን ወቅታዊ ችግር አስመልክቶ በጉባኤው ሰፊ ውይይት የተደረገበት መሆኑን ገልፀዋል።

በዚህም በሀገሪቱ በተከሰተው ወቅታዊ ችግር በቤተክርስቲያን እና በክርስትያን ወገኖች ላይ የደረሰው ግፍና መከራ እንዲቆም፣ የታሰሩ ካህናትና ምዕመናን ጉዳያቸው እየታየ ከታሰሩበት እንዲፈቱም ጠይቀዋል።

ከህዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘም የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አካባቢያዊ ጦርነት እንዲነሳ ያስተላለፉትን መልዕክት ያወገዘው ሲኖዶሱ፣ ኢትዮጵያን በቅኝ ግዛት ወይም በሞግዚትነት ለማስተዳደር የተደረገ ሙከራ በመሆኑ የዓለም መንግስታትና ህዝቦች ይህን ድርጊት እንዲቃወሙም ቅዱስ ሲኖዶሱ ጥሪ አቅርበዋል።

(በአድማሱ አራጋው)

By Eyasu Esayas

Entrepreneur, Writer, Business advocate and Teacher. Nice to have every soul on board. Eyasu do adore the HUMAN Nature. Join the Wonderful Team.

Say Something