Ethiopia Special report Amharic :በሠራዊታችን ላይ የተፈፀመን እጅግ ዘግናኝና አረመኔያዊ ተግባር፤ መላው ኢትዮጵያዊያን እንዲያውቁት ሼር አድርጉት‼ (ልዩ ሪፖርታዥ)በሠራዊታችን ላይ የተፈፀመን እጅግ ዘግናኝና አረመኔያዊ ተግባር፤ መላው ኢትዮጵያዊያን እንዲያውቁት ሼር አድርጉት‼ (ልዩ ሪፖርታዥ)

👉ሰሜን ዕዝ እንዴት ሊጠቃ ቻለ:– ይህን ከታማኝ ምንጫችን ያገኘነውን፣ በሠራዊታችን ላይ የተፈፀመን እጅግ ዘግናኝና አረመኔያዊ ተግባር፤ መላው ኢትዮጵያዊያን እንዲያውቁት ሼር አድርጉት‼ (ልዩ ሪፖርታዥ)

የትሕነግ ጁንታ ቡድን በተላላኪዎቹ አማካኝነት እጅግ ከፍተኛ ውድመቶችን እያደረሰ ለንጹሃን ዜጎች ሞት ምክንያት ቢሆንም፤ እቅዶቹ ብዙም ነፍስ ሳይዘሩ ከ20 ጊዜ በላይ በመከላከያ ሠራዊታችን ከሽፈውበታል፡፡ ጁንታው መከላከያ ሠራዊታችንን ለመከፋፈል ብዙ ሞክሯል፡፡ የሐሰት ወሬ በስፋት ረጭቷል፡፡ ይህም ከሽፎበታል፡፡ በመጨረሻም የዚህን ቡድን ሁሉንም ሴራ በየቦታው ያለእረፍት እየተወነጨፈ በሚያመክነው የመከላከያ ሠራዊታችን አካል በሆነው የሰሜን ዕዝ ሠራዊት ላይ እጅግ የከፋ በጭካኔና በአረመኔነት የተሞላ ፋሽስታዊ ድርጊትና ጥቃት ፈጽሟል‼

በትግራይ ክልል ከሕዝቡ ጋር ሆኖ ሰብል በመሰብሰብ የሚረዳውን፣ የአምበጣ መንጋ በተከሰተበት ወቅት ‘ሕዝቤ ነው’ ብሎ በመከላከል ስራ ተሰማርቶ ሲያግዝ በነበረው የሰሜን እዝ ሠራዊት ላይ ከበባ በማድረግ፤ በትሕነግ ጁንታ ለእኩይ ዓላማ የሰለጠነው የትግራይ ክልል ልዩ ኃይልና ሚሊሽያ የከፈተው ጦርነት በእናት ጡት ነካሽነት የተፈጸመ ታላቅ የክህደት ወንጀል ነው፡፡ ሕወሀት የደፈረው የገደለው የሀገሩ ጠባቂና መኩሪያ የሆነውን የሰሜን ዕዝን ሠራዊት አባላት ብቻ አይደለም–መላው ኢትዮጵያንን እንጂ‼ ያም ሆኖ፤ የትሕነግ ጁንታ በውስጥ ከሃዲዎቹ አማካኝነት ሠራዊታችን ላይ በታሪካችን ታይቶ የማይታወቅ ዘግናኝ ድርጊት ፈፅሟል፦

1—በሰሜን እዝ ውስጥና በሌሎችም የጦር ክፍሎች ውስጥ በመደበኛ የሠራዊት አባልነት ይሰሩ የነበሩ በዕዙ ካምፕ (መቀሌ) በወታደራዊ ጦር ሰፈሮች ውስጥ ከሠራዊቱ ጋር አብረው ለረዥም ጊዜ የኖሩና የሰሩ በተለያየ የማዕረግ ደረጃ ላይ ይገኙ የነበሩ የትግራይ ተወላጅ የሆኑ አባሎች ከውስጥ ሆነው ውጭ ካለው የትሕነግ አመራርና የልዩ ኃይል አዛዦች እንዲሁም ደህንነቶች ጋር በምስጢር በማሴር ያልተጠበቀና ያልተገመተ አደጋ በሰሜን ዕዝ ላይ አድርሰዋል‼

2—ሀገር ሰላም ብለው በሰሜን ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ (መቀሌ) የነበሩትን መኮንኖችና ወታደሮች መሳሪያቸውን ለማንሳት፣ ለመገመትም ሆነ ለመጠራጠር እንኳን ጊዜ ሳይኖራቸው የሠራዊቱ አባላት የሆኑት የትግራይ ተወላጆች ሠራዊቱን ከውጭ በትግራይ ልዩ ኃይል አስከብበው እነሱ ደግሞ ከውስጥ ሆነው ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም ከምሽቱ 4 ሰዓት ላይ ተኩስ ከፍተው በተኙበት ጨፍጭፈዋቸዋል‼

3— የትሕነግ ጁንታ ቡድን አመራሮች በሰጡት ትዕዛዝ መሰረት፤ ልዩ ኃይሎቹ የሠራዊቱን አመራሮች እየገደሉ ሰሜን እዝ ውስጥ ያሉትን ትግርኛ ተናጋሪዎች በሙሉ የወደደውንም ያልወደደውንም ወደ ልዩ ኃይል በመደባለቅ የኢትዮጵያን መከላከያ ሠራዊት እንዲወጋ አደረጉት‼ ካምፕ ገብተው ከትግርኛ ተናጋሪ ብሔር ውጭ የሆነውንና ከጭፍጨፋው የተረፉትን የመከላከያ ሠራዊት አባላት በሙሉ ሰብስበው የለበሱትን ወታደራዊ ሬንጀር ልብስ አስወልቀው፣ ትጥቃቸውን አስፈትተው፣ ወታደራዊ ጫማቸውን አስወልቀው በባዶ እግራቸው ሆነው ወደ ምትሄዱበት ሂዱ በማለት በተኗቸው‼አሁን እነዚህ የሠራዊት አባላት የት እንደደረሱ አይታወቅም፡፡ ይሄ የሆነው በመጀመሪያው ቀን ነው–ጥቅምት 24 /2013 ምሽት ላይ፡፡ ይህን የፈፀሙት ዕዙን ከበው ጥበቃ ላይ የነበሩትን ወታደሮች በቦምብ ገድለው ከገቡ በኋላ ነው። ይህም በገዛ ወገናቸው ላይ የተፈፀመን አረመኔነት ጥግ የሚያሳይ ነው‼

4—ሌላው ሰቅጣጭና በጣም ዘግናኙ አረመኔነት፤ አዛዥና ምክትሉ ሆነው የሚሰሩት ስራ ስለሚያገናቸው ብዙ ጊዜ ምሳ አብረው ይበሉ ነበር፡፡ በዚያን ዕለት ትግርኛ ተናጋሪው አዛዥ (ኮሎኔል) ምክትሉን የአማራ ተወላጅ (ኮሎኔል)፣ አብሮት ለረዥም ጊዜ የሰራውን ጓደኛውን ከሰው መሐል ጠርቶ ‘ና ምሳ እንብላ’ ብሎ በመውሰድ (ይሄኛው እንደ ሌላው ግዜ መስሎት አልተጠራጠረም እሺ ብሎ አብሮት ይሄዳል) ሆኖም በመንገድ ላይ በጥይት መትቶ ገድሎታል። ይህም የሆነው የመጀመሪያው ከላይ በጠቀስኩት የመጀመሪያ ቀን ነው‼

5—-እንደገና በዚያኑ ዕለት በ31ኛ ክፍለ ጦር ውስጥም አስደንጋጭ ሁኔታ ተከሰተ፡፡ የክፍለጦሩ ምክትል አዛዥ ትግርኛ ተናጋሪ ነው። ኮሎኔል አብርሃ ይባላል፡፡ አዛዡ ኮሎኔል ሲሳይ ሲሆን የአማራ ተወላጅ ነው፡፡ ኮሎኔል አብርሃ በአዛዡ ላይ ድንገት ተኩስ ይከፍትበታል፡፡ ሁለቱም የመታኮሻ ቦታ ይዘው ሲታኮሱ ይቆዩና ኮሎኔል ሲሳይ ኮሎኔል አብርሃምን ገደለው፡፡ ኮሎኔል ሲሳይ የሚመራውን ጦር ይዞ እየተታኮሰ ከበባውን ጥሶ ወጣ፡፡ የትሕነግ ስግብግብ ቡድን እንዲህ ዓይነት እጅግ አረመኔና ጨካኝ ነው፡፡ የሰራዊቱን ቁልፍ አመራሮች ውስጥ ባሉት የትግራይ ተወላጆች  እንዲገደሉ ትዕዛዝ የተሰጠው በሰው በላው የትሕነግ አመራር ነው፡፡ አዛዦች ገድለው ቦታውን በትግራይ አመራሮች በማስያዝ ሠራዊቱን እንቆጣጠራለን፤ እንመራለን ወይንም ሠራዊቱ አመራር ሲያጣ ይበተናል ብለው ነበር ያቀዱት፡፡ ግና አልተሳካም‼

6— የትግራይ ልዩ ኃይል አባላት ከውስጥ ትግሪኛ ተናጋሪ ተባባሪዎቻቸው ጋር በመሆን የሰሜን ዕዝን ቢሮ ከውጭ ከከበቡ በኋላ፤ የሰራዊቱ አባላት የነበሩትና ሰራዊቱ ያልጠረጠራቸው በካምፑ ውስጥ የነበሩት ትግርኛ ተናጋሪዎች ከውስጥ ተኩስ ከፍተው ሠራዊቱን በጥይት ሲደበድቡ፤ ከውጭ  ከቦ ሲጠባበቅ የነበረው የትግራይ ልዩ ኃይል በዕዙ ጥበቃ ላይ የነበሩ ወታደሮችን በቦምብ በመግደል ግቢ ገብተው የምክትል አዛዡን መኪና እያየ ነድተው ወሰዱት፡፡ እጅ ስጥ አሉት። እርሱም “ለእናንተ እጄን አልሰጥም” አለ፡፡ “አንድ ክላሽ አንድ ሽጉጥ ይዣለሁ፡፡ እስከ መጨረሻው እዋጋለሁ፡፡ አንድ ጥይት ስትቀር ለእራሴ አደርጋታለሁ” እያለ ሲናገር የስልክ ግንኙነት ነበር፡፡ ግን ወዲያውኑ ተቋረጠ‼

7—ይሄ ሁሉ ወንጀል የተፈጸመው ሠራዊታችን “ሰላም ነው፤ ሀገሬ ነው፤ ወገኖቼ ናቸው፤ ምንም የጦርነት ሁኔታ የለም” ብሎ በሰላም ውሎ ገብቶ በተኛበት ነው፡፡ የትግራይ ልዩ ኃይልና በሠራዊቱ ውስጥ ያሉት የትግራይ ተወላጆች በምስጢር መክረው ተዘጋጅተውበት ነው ያልታሰበ ወረራ ከውስጥና ከውጭ ሆነው ተቀናጅተው በማድረግ በጦር ሰፈሩና በመከላከያ ሰራዊት አባላት ላይ ጭፍጨፋ ያካሄዱት፡፡ ዋናውን ሚና የተጫወቱት በሠራዊቱ ውስጥ የነበሩት ትግርኛ ተናጋሪዎች ናቸው‼

8—የሰሜን ዕዝ ወታደራዊ ቀጣናው ሰፊ ስለሆነ ሠራዊታችን በተለያዮ ቦታዎች ተበታትኖ ነው ድንበር የሚጠብቀው፡፡ መቀሌ ከተማ ያለው የሰሜን ዕዝና የሠራዊቱ አባል፤ ሀገሬ ነው ሕዝቤ ነው ሰላም ነው ምንም የለም ብሎ ነበር የነበረው፡፡ ግማሹም የቀለም ትምህርት ዩኒቨርሲቲ የሚያስተምር ነበር፡፡ቀን ሲሰራ ውሎ ማታ ደክሞት ካምፕ ገብቶ በተኛበት ነው ይሄ ሁሉ የግፍ ግፍና በአረመኔነት የተሞላ ወንጀል የተፈጸመበት፤ በጥይት የተደበደበው‼

9—-አብዛኛውን ግፍና የግፍ ግፍ የሆነ ወንጀል የፈጸሙት ከሠራዊቱ ጋር አብረው የነበሩ ትግርኛ ተናጋሪ የሠራዊት አባል ናቸው‼አብሮ ጦር ሜዳ የተሰለፈውን፣ አብሮ የሚዋደቀውን፣ አብሮት የሚበላውንና የሚጠጣውን፣ እነሱን ለመጠበቅ ከተለያየ የኢትዮጵያ ክፍል ተውጣጥቶ የሠራዊት አባል ሆኖ በእናት ሀገር ጥበቃ ተሰማርቶ በሚገገኘው ጓዶቻቸው ላይ እንዲህ አይነት በከሃዲነት የተሞላ ጭፍጨፋ አድርገዋል፡፡ ይህን የመሰለ ፋሽስትነት አረመኔነት በታሪክ ታይቶም ሆነ ተሰምቶ አይታወቅም‼

10— የትግራይ ልዩ ኃይልና ሚሊሽያ ይሄን ሁሉ በግፍ የተሞላ ወንጀል በአዛዡ በእነ ታደሰ ወረደና በሌሎችም እቅድ አውጪነት እንዲሁም መሪነት ትዕዛዙን ከፈጸሙ በኋላ የስልክም ሆነ ሌላ ግንኙነት እንዳይኖር አጠቃላይ ግንኙነቱን ዘግተውታል፡፡ የመከላከያ ሠራዊታችን አንዱ ከሌላው ጋር እንዳይገናኝ የግንኙነት ሬድዮኑን አበላሽተውታል፡፡ በአጠቃላይ ከአዲስ አበባም ሆነ  በሰሜን ዕዝ ውስጥ ባሉ የሠራዊት ክፍሎች መካከል ምንም ዓይነት የመልእክትም የሬድዮም ግንኙነት እንዳይኖር ተደርጓል። ይህ የተፈፀመውም በውስጥና በውጭ በተቀናጀ ሴራ ነው‼

11— ከማክሰኞ (24/02/2013 ዓ.ም) እስከ ሐሙስ (26/02/2013 ዓ.ም) ድረስ ምንም ዓይነት ግንኙነት አልነበረም ፡፡ ይህን ያደረጉት ከበላይም ሆነ በተለያዩ የጦር ክፍሎች ውስጥ ምንም አይነት በሬድዮ የሚደረግ ግንኙነት እንዳይኖር ፤ አንዱ የጦር ክፍል ለሌላው እገዛና ትብብር እንዳያደርግ የትግራይ ክልል ልዩ ኃይልና የሚሊሽያ ሠራዊት በተለያየ ቦታዎች የከበባቸውን የሰሜን ዕዝ የጦር ክፍሎች (ሜካናይዝድ፣ መድፈኛና ታንከኛ እንዲሁም የሚሳይል ምድብተኛ) የሆኑ ጀሠራዊት ክፍሎች እርስ በእርስ በማይገናኙበት ሁኔታ ከቦ በመደምስስ መሳሪያዎቹን ለመዝረፍና ለመታጠቅ ነበር፡፡ ሁሉም የሰሜን እዝ የጦር ክፍሎች በያሉበት ቦታ 360 ዲግሪ  ለወያኔ እጃችንን አንሰጥም ብለው እጅግ በላቀ ቆራጥነትና አስደናቂ ጀግንነት ተዋግተው መስዋእትነት ከፍለው ጠላትን አራግፈውታል‼ በዚህም ከእኛ በላይ ጀግና፣ ወታደራዊ እውቀት ያለው የለም ባዮቹ የከሀዲዎቹ የሀገር ሻጮቹ የደደቢት ሽፍቶችና የፋሽስቶቹ ሴራ ወታደራዊ እቅድ ሙሉ በሙሉ አፈር ግጦ ከሽፏል‼

12—-የሀገር መከላከያ ሠራዊትን እንደ ጠላት ጦር በመቁጠር በያለበት የመከላከያ ይዞታው ላይ የትግራይ ልዩ ኃይልና ሚሊሺያ 360 ዲግሪ ከቦት በነበረበት ወቅት፤ ምንም ዓይነት የሬድዮ ግንኙነት ስላልነበረ ሠራዊቱ  በየቦታው ተኩስ አለ የሚል ነገር ሰምቷል፡፡ ኮሎኔል ያሲን የመካናይዝድ አዛዥ ነው፡፡ እሱን ከበው በሠራዊቱ ውስጥ ያሉት የሠራዊቱ አባላት የሆኑ የትግራይ ተወላጆች ሌላ ቦታ እንዳደረጉት ሁሉ እጅህን ስጥ አሉት፡፡ እነሱን እንዳለ ረፈረፈና ሜካናይዝድ ጦሩን ይዞ እየተዋጋ ከፊቱ የተጋረጠውን ሁሉ እየደመሰሰ ጥሷቸው ማዶ ተሻገረ፡፡ ኃይሉን መልሶ አደራጅቶ በመመለስ በአሁኑ ሰአት እየተዋጋቸው ይገኛል፡፡ በዚህ ያልተጠበቀ ለማመንም በሚያስቸግር ክስተት ውስጥ ብዙ ቆራጥ የጦር ሜዳ ጀግኖች ኢትዮጵያውያን ተፈጥረዋል፡፡ ተወልደዋል፡፡

13—ሌላው ጀግና ብርጋዲየር ጄኔራል ሙሉዓለም ነው፡፡ የ5ተኛ ሜካናይዝድ ክፍለጦር አዛዥ። ዳንሻ ላይ የትግራይ ልዩ ኃይልና ሚሊሺያ ከበበው፡፡ እጅህን ስጥ አሉት፡፡ “ደሜን ትጠጣታለህ እንጂ ለአንተ ለወያኔ እጄን አልሰጥም” ብሎ መታኮስ ጀመረ፡፡ አብረውት የነበሩት የጄኔራሉ ጠባቂዎች የትግራይ ተወላጅ የሆኑ የመከላከያ ሠራዊታችን አባል ናቸው፡፡ “ከአንተ ጋር እንሞታለን” ብለው የሜካናይዝድ ጦሩም ገትሮ ይዞ 48 ሰዓታት (ሁለት ቀናት) ያለማቋረጥ ተዋጉ፡፡ ከሁሉም በላይ አስገራሚው ነገር፤ ስንትና ስንት ከሃዲዎችና ባንዳዎች በታዩበት ሁኔታ ውስጥ ጄኔራሉና ጦሩ ተከበው እያሉ የትግራይ ልዩ ኃይል ማይክራፎን በመጠቀም፤ እነዚያን የትግራይ ተወላጅ የሆኑ የጄኔራሉን ጠባቂዎች “ግደሉትና ኑ! ለሀገራችሁ ለትግራይ ተዋጉ” እያሉ ሲቀሰቅሷቸው፤ እነርሱ ደግሞ እናንተን እናጠፋችኋለን እንጂ ማንንም አንገልም ብለው በጀግንነት መዋጋታቸው ነው‼

በዚህ ሁኔታ ላይ እያሉ ሠራዊታችን ደረሰላቸው፡፡ በአካባቢው ከቧቸው የነበረውን የትግራይ ልዩ ኃይልና ሚሊሽያ ሙሉ በሙሉ ደምስሰው፤ አሁንም ወደፊት በመገስገስ ላይ ይገኛሉ፡፡ አዛዡም ሠራዊቱም የጀግና ጀግና ናቸው‼ትላንት በ28/02/2013 አዲግራት አካባቢ የሚገኝ የትግራይ ልዩ ኃይል መሳሪያ ማከማቻ ዴፖ ሙሉ በሙሉ ያወደመው አየር ኃይላችን፤ ዛሬም በተመረጠ ዒላማ ላይ የተሳካ ድብደባ አካሂዷል‼እነዚህን ለጆሮ የሚከብዱ ዘግናኝ ወንጀሎችን የፈፀመው የትሕነግ ስግብግብ ጁንታ ቡድን ከተደበቀበት የቀበሮ ጉድጓድ ማንቁርቱን ይዞ ሕግ ፊት ለማቅረብ፤ ጀግናው የመከላከያ ሠራዊታችን ጠላቶቹን እየደመሰሰ ወደፊት በመገስገስ ላይ ነው‼

ድል ለጀግናው ሠራዊታችን‼

#ጃተማ_አባቢያ

#የኢትዮጵያ_ክንድ

Say Something