Ethiopia new updates-ፅንፈኛው የህወሓት ቡድን በከተሞች ጥቃት እንዲፈፅሙ ያሰማራቸው ግለሰቦች በቁጥጥር ስር እየዋሉ ነው- ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ፅንፈኛው የህወሓት ቡድን በከተሞች ጥቃት እንዲፈፅሙ ያሰማራቸው ግለሰቦች በቁጥጥር ስር እየዋሉ መሆኑን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል እንደሻው ጣሰው በሰጡት መግለጫ ፅንፈኛው የህወሓት ቡድን አዲስ አበባን ጨምሮ በአገሪቱ የተለያዩ ከተሞች ጥቃት ለማድረስ ያሰማራቸው ግለሰቦች በቁጥጥር ስር እየዋሉ ነው።

ግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር እየዋሉ ያሉት በህብረተሰቡ ትብብርና ጥቆማ እንዲሁም በፀጥታ ሃይሉ ጠንካራ ክትትል መሆኑንም ገልጸዋል።

የህወሓትን እኩይ ተግባር ለማክሸፍ በቀጣይም የተጀመረው ጠንካራ ስራ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ኮሚሽነር ጀነራል እንደሻው ማረጋገጣቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

Say Something