አዲስ አበባ፣ ሕዳር 3፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠቅላይ አቃቤ ህግ በተለያዩ ወንጀሎች የጠረጠራቸውን የ39 ግለሰቦች ያለመከሰስ መብት እንዲነሳ ያቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ በሙሉ ድምጽ አፀደቀ።

በዚህም መሰረት፦ 

ዶክተር ደብረጸዮን ገብረሚካኤል

አቶ አስመላሽ ወልደስላሴ

አቶ አባይ ፀሃዬ 

ዶክተር አምባሳደር አዲስ ዓለም ቤሌማ 

አቶ ጌታቸው ረዳ

አቶ አፅበሃ አረጋዊ

አቶ ገብር እግዚአብሄር አርአያ እና ሌሎችም የህወሓት ተወካዮች ላይ የቀረበውን ያለመከሰስ መብት የውሳኔ ሀሳብ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል። 

ግለሰቦቹ የተጠረጠሩበት ወንጀሎችም  ጦር መሳሪያ ይዞ በማመፅ፣ የሀገር መከላከያን በመውጋት እና በሌሎችም ተያያዥ ወንጀሎች ዋና አድራጊነት ነው መሆኑ ታውቋል።

By Eyasu Esayas

Entrepreneur, Writer, Business advocate and Teacher. Nice to have every soul on board. Eyasu do adore the HUMAN Nature. Join the Wonderful Team.

Say Something