Addis Ababa news: ጠቅላይ ሚንስትር አብይ የሸገር ፓርክ ምረቃ ስነ-ስርአት ከባለቤታቸው ጋር ተገኝተዋል።

በመከላከያ ማርሽ የደመቀው የሸገር ፓርክ ዛሬ በይፋ በመመረቅ ላይ ይገኛል። የተለያዩ እንግዶችና የከፍተኛ ፖለቲካ ሰዎች የታደሙበት የሚረቃ ስርአት ከአዲስ አበባ በቀጥታ ስርጭት እየታየ ስሆን የአዲስ አመት ዋዜማ እና ኮሮና በሽታ ጋር ተያይዞ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶታል።

የትግራይ ክልላዊ መንግስት የፌደራል መንግስት ያስተላለፈውን ውሳኔ አሻፈረኝ በማለት እያካሄደ ይገናኛል። የህገ-መንግስታዊ ፌደራል ስርአትን ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባው፣ የትግራይ ክልል ምርጫ በተባለበት ጊዜ ብከናወንም የቀጣዩ የክልሉ ዕጣ ፋንታ አልታወቀም።

በፖለቲካ፣ በግጭት እና በዕልቂት እየተፈተነ ያለው የዶ/ር አብይ መንግስት ታርካዊ የፖለቲካ አጣብቅኝ ውስጥ ይገኛል። ይህ በ 27 አመት ውስጥ የሃገርቱን ህዝብ በዘር ያከፋፈለው የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር (ህወሓት) ፣ ዛሬም በልዩነት አቋም የፀና ይመስላል።
ዛሬ የክልል ምርጫ ያለምንም የፌደራል ስርአት እውቅና ከተሰጠው፣ ነገ ‘ተገንጥሎ’ ለመውጣት ተመሳሳይ መሆኑ ግልፅ ነው። የህግና ህገ- መንግስት ስርአት በሰከነ እና ሃገርን በማይጎዳ መልኩ ማድረግ መርህ ፖለቲካ መሆን አለበት። ከሁሉም ቅድምያ መሰጠት ያለበት የህዝብ ደህንነት እና ህገመንግስታዊ ስርአት ብቻ ነው።

“የትግራይ መንግስት የሚያካህደው ምርጫ ህገመንግስታዊ መሰረት የለውም፣ ህገምወጥ ነው።’: ሲል የፌደረሸን ምክር ቤት መወሰኑ ይታወቃል።

Say Something