👉የተከበርከው የትግራይ ህዝብ ሆይ የስግብግቡን ጁንታ ግብአተ መሬት ለመፈፀም በመጨረስ ላይ እንገኛለን፤
👉ጁንታው ቡድን በሁሉም አቅጣጫ ተከቧል፤ መውጫና መግቢያ አጥቶ ታፍኖ የሞት ጣር ላይ ይገኛል፤
👉ባሁኑ ሰአት ስግብግቡ ጁንታው አመራር ለመስጠት በማይችልበት ደረጃ ደርሶ ይገኛል፤ ልጆችህ ያለ ምግብ እና ውሃ የሞት እራት እየሆኑ ነው ስለዚህ ልጆችህ ሂወታቸውን እንዳይሰጡ በፍጥነት አድን፤
👉የልጆችህ ሞት የጁንታውን እድሜ ለሰአታት ወይም ለቀናት ከማራዘም ውጪ ምንም ትርጉም የለውም፤
👉ሰው ለሃገር እና አለማ እንጂ ለጥፋት ቡድን ብሎ ሊሞትና አካሉ ሊጎድል አይገባም፤
👉ከትግራይ ህዝብ በላይ የጦርነት አስከፊነት የሚያውቅ የለም፤ ጁንታው ቡድን ለራሱ አይሞትም አካሉም አይጎድልም ስለዚህ የልጆችህ ደም ለጁንታው ቁማር መጫወቻ መሆን የለበትም፤
👉 የልጆችህን ውድ ህይወወት ለማትረፍና ከአንበጣ የቀረውን እህልህን ወደ መሰብሰብ እንድትመለስ ተጋግዘን ጁንታውን ቡድን ቶሎ ልንጨርሰው ይገባል ብዬ ጥሪዬን አቀርባለሁ፤
👉የተከበርከው የትግራይ ህዝብ ስግብግቡን ጁንታ ቶሎ መተን ወደ ልማታችን ልንመለስ ይገባል ስለዚህ የወጣት ልጆችህን ህይወት ቶሎ አድን፤ እያደረከው እንዳለሀውም መከላከያ ሰራዊትን አግዝ፤
👉በመስዋእትነት የገነባሀትን ኢትዮጵያ አሁንም በማዳን ታሪክህን እንድታድስ ውድ አገርህ ጥሪ አድርጋልሃለች፤
👉በተለያየ የአመራር እርከን ያላችሁ ሲቪል መሪዎች ያለን ተቃርኖ በህወሓት ተሰግስገው ካሉ ጥቂት ሰዎች ጋር ብቻ ስለሆነ ራሳችሁን ከዚህ ጁንታ እንድታርቁ ጥሪ ቀርቦላችኋል፤
👉 መላው የትግራይ የፀጥታ አባላት በሙሉ ባለፉት ጥቂት ቀናት የገጠማችሁን አይታችኋል የስርአቱ ተጠቃሚዎች ወደ ሞት እያሰገቧችሁ ነው፤ እነሱ እየበሉ እየጠጡ እየተኙ እናንተ ግን በባዶ ሆዳችሁ የጥይት እራት እየሆናችሁ ነው፤
👉ጁንታው ቡድን አይደለም ደማቸውን ለመስጠት ሂወታቸውን ለመገበር ይቅርና የተኩስ ድምፅ ለመስማት እንኳ አይፈልጉም፤ ታድያ ለየትኛው አለማ ነው ወጣትነታችሁ በከንቱ የምታጠፉት፣ ለምን ትግራይን የወላድ ድሃ ታደርጓታላችሁ፣ ለምንስ ጉልበታችሁን ልማት ላይ አታውሉትም፣
👉ለዚህ ቀናት የቀሩት ጁንታ ቡድን ብላችሁ ህይወታችሁን ልትገብሩም ሆነ ደማችሁን ልታፈሱ በፍፁም ኣይገባም፤
👉 እጃቹህ ለመከላከያ በመስጠት አገራችሁ የሰጠቻችሁን እድል ሳያመልጣችሁ በሁለት ሶስት ቀናት ራሳችሁን አድኑ፤
ኢትዮጵያ በእውነተኛ ልጆችዋ ታሸንፋለች!