የአፍሪካ ህብረት ኢትዮጵያዊ የደህንነት ኃላፊውን ከስራ ማሰናበቱን ገለጸ።
የህብረቱ የደህንነት ኃላፊ የነበሩት ሜጀር ጄነራል ገ/እግዚአብሔር መብራቱ መለስ ኢትዮጵያ የታማኝነት ጥያቄ ስላነሳችበት ከስራው እንዲሰናበት ማድረጉን የአፍሪካ ህብረት አስታወቀ።
የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መሀመት ኅዳር 2 ቀን 2013 ዓ.ም ለሜጀር ጄነራል ገ/እግዚአብሔር መብራቱ መለስ የስራ ስንብት ደብዳቤ መስጠታቸው ተገልጿል፡፡
ውሳኔው የኢትዮጵያ መንግስት በግለሰቡ እምነት እንደሌለው ከአንድ ቀን በፊት ካስታወቀ በኋላ የመጣ መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
Please follow and like us: