የጽንፈኛው የህወሓት ቡድን መሪዎች ቤተሰቦቻቸውን ወደ ሌላ ሀገር በማሸሽ የትግራይ ልዩ ኃይልን ወደ ጦርነት በማሰለፍ እያደረገ ያለው የሞት ሽረት ትግል ተገቢ ባለመሆኑ ከመከላከያ ጎን እንዲሰላፍ የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ትዴፓ) ጥሪ አቀረበ፡፡  

ልዩ ኃይሉ አንድነቱን አጠናክሮ ከመንግስት ጎን መሰለፍ እንዳለበትም መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

ህገ-መንግስቱን መጣስ ሀገርን መካድ መሆኑንም ትዴፓ ዛሬ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል፡፡

በሀገሪቱ የተደረገው ስር ነቀል ለውጥን ለመቋቋም ሸሽቶ ከተቀመጠው ቡድን የሞት ሽረት እያደረገ እንደሚገኝ የትዴፓ ሊቀ መንበር ዶ/ር አረጋዊ በርሄ ተናግረዋል፡፡  

ዶ/ር አረጋዊ የመከላከያ ሰራዊቱ እነዚህን ፀረ ሰላም፣ ፀረ አንድነት፣ ፀረ ህዝብ  የሆኑ ቡድኖች ሳይደመሰስ ወደ ኋላ እንደማይመለስ እምነት አለኝም ብለዋል፡፡

(በስመኝ ፈለቀ)

Please follow and like us:

By Eyasu Esayas

Entrepreneur, Writer, Business advocate and Teacher. Nice to have every soul on board. Eyasu do adore the HUMAN Nature. Join the Wonderful Team.

Leave a Reply

RSS
Follow by Email
Twitter
YouTube
Pinterest
LinkedIn
LinkedIn
Share
Instagram
Telegram
WhatsApp