የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ኢንዶክትሪኔሽን ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጄነራል መሀመድ ተሰማ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ትግራይ የራሱ የሆነ የአየር ኃይል እንደሌለው ገልጸዋል፡፡

የኢፌዴሪ አየር ኃይል የተሰጠውን ተልዕኮ እየተወጣ መሆኑን የገለጹት ሜጀር ጄነራሉ፣ እየተሰራጨ ያለው ዘገባ በካሜራ የተቀነባበረ የውሸት መረጃ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡ የአየር ኃይሉ ገበያዎችን፣ የህዝብ መሰብሰቢያ ቦታዎችን እና ከተማዎችን መምታት ዓላማው እንዳልሆነም በመግለጫቸው አመልክተዋል፡፡

የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት የሁመራ ሱዳን መንገድን፣ ማይዳሊ፣ ዳንሻ፣ ባዕከር እና ሌጉዱ አካባቢዎችን የተቆጣጠረ ሲሆን፣ ህወሓት እነዚህ ቦታዎች በቁጥጥር ስር አልዋሉም እያለ ያለው መረጃ የተሳሳተ ነው ብለዋል፡፡

የኢፌዴሪ አየር ኃይልም ሆነ መከላከያ ሰራዊት በውጊያው መከፈል ያለበትን መስዋዕትነት ይከፍላል፤ ተልዕኮንም ይፈጽማል ሲሉም ሜጀር ጄነራል መሀመድ ተሰማ በሰጡት መግለጫ አክለዋል፡፡

(በትዕግስት ዘላለም)

Please follow and like us:

By Eyasu Esayas

Entrepreneur, Writer, Business advocate and Teacher. Nice to have every soul on board. Eyasu do adore the HUMAN Nature. Join the Wonderful Team.

Leave a Reply

RSS
Follow by Email
Twitter
YouTube
Pinterest
LinkedIn
LinkedIn
Share
Instagram
Telegram
WhatsApp