አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በህወሓት ውስጥ ያለው ቡድን በትግራይ ክልል በሚገኙ የባንክ ቅርንጫፎች ላይ ዘረፋ እየፈፀመ መሆኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስታውቋል።
የትግራይ ሕዝብና የሚመለከታቸው አካላት ባንኮቹ እንዳይዘረፉ የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ባንኩ ጥሪ ማቅረቡን ኢቢሲ ዘግቧል።
አሁን ባለው ሁኔታ በክልሉ የሚገኙ ባንኮች አገልግሎት መስጠት ስለማይችሉ ተዘግተው እንዲቆዩ ነው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ያሳሰበው።
Please follow and like us: