ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ መንግስት በትግራይ የጀመረው ሕግ የማስከበር እርምጃ ዓላማው ስግብግቡን የመቀሌ ጁንታ ለሕግ ተገዥ የማድረግና ሕገ መንግስታዊ ስርዓትን ማስጠበቅ መሆኑን አስታወቁ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ገጻቸው ይፋ እንዳደረጉት እርምጃው ከማንም በላይ ሰፊውን ትግራዋይ ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው ብለዋል።
መንግስት የወሰደውን እርምጃ ተከትሎ ወንድምና እህት ትግራዋይን ማንነታቸውን ያማከለ ለምንም አይነት ሕገወጥ ድርጊት ሰላባ እንዳይሆኑ የማድረግ ኃላፊነት በሁሉም ኢትዮጵያዊ ዘንድ እንዳለበት ከአደራ ጭምር ጋር አሳስባለሁ ብለዋል።
Please follow and like us: