አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29፣ 2013 🙂 በህወሓት ውስጥ ባለ ቡድን የሚደርስባቸው የሚደርስባቸውን አፈና እና እንግልት የተቃወሙ 41 የሚሊሻ አባላት ወደ አብርሃጂራ ከተማ ገቡ።

የሚሊሻ አባላቱ ነዋሪነታቸው በጸገዴ ወረዳ ሲሆን ወደ አማራ ክልል የገቡት በትግራይ ክልል ለሚገኘው በህወሀት ውስጥ ላለ ቡድን  መጠቀሚያ ላለመሆን ነው ብለዋል።

በዚህ ቡድን ላይ መንግስት የጀመረውን ህግ የማስከበር እርምጃ በመደገፍና ከጸጥታ አካሉ ጋር በጋራ በመሆን የማገዝ ፍላጎቱ እንዳላቸውም ለአብመድ ተናግረዋል።

የትግራይ ህዝብም እንደ ሌሎቹ ወንድም ህዝቦች ነጻነቱን ማረጋገጥ እንዲችል ከፌዴራል መንግስት ጎን እንዲቆም መልዕክት አስተላልፈዋል።

በምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ ወደ አብርሃጂራ ከተማ 41 የሚሊሻ አባላት እንደገቡም የምዕራብ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ደሳለኝ ጣሰው ገልጸዋል።

በቀጣይም የልዩ ሃይል እና የሚሊሻ አባላት ቢገቡ ለመቀበል መዘጋጀታቸውን እና በሁለቱ ህዝቦች መካከል ያለውን አብሮነት አሁንም እንዲቀጥል እንደሚሰራ አስተዳዳሪው ተናግረዋል።

Please follow and like us:

By Eyasu Esayas

Entrepreneur, Writer, Business advocate and Teacher. Nice to have every soul on board. Eyasu do adore the HUMAN Nature. Join the Wonderful Team.

Leave a Reply

RSS
Follow by Email
Twitter
YouTube
Pinterest
LinkedIn
LinkedIn
Share
Instagram
Telegram
WhatsApp