የመከላከያ ሠራዊት ዳንሻን፣ ባከርን እና ከሽራሮ አስከ ሽሬ ያሉ አካባቢዎችን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠሩን የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ምክትል ኤታማዦር ሹም እና የኦፕሬሽን ዘርፍ ኃላፊ ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ አስታወቁ። 

ለኢትዮጵያ ነቀርሳ የሆነው ከሀዲው የህውሓት ቡድን ካልተደመሰሰ ሀገር ሰላም እንደማትሆንም ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹሙ ገልፀዋል። 

ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ የመከላከያ ሠራዊቱን የግዳጅ እንቅስቃሴ አስመልክተው እንዳስታወቁት፣ የመከላከያ ሠራዊቱ ዳንሻን፣ ባከርን እና ከሽራሮ አስከ ሽሬ ያሉ አካባቢዎች ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሮ ወደ ፊት እየገሠገሠ ይገኛል።

መከላከያ በከሀዲ ቡድኑ እጅ ያሉ ከባድ መሳሪያዎች ሙሉ በሙሉ ማውደሙን አመልክተው፣ እንደ ተምች በየቦታው ሠራዊቱን የከበበውን ኃይል እያራገፈ መሆኑን ጠቁመዋል። ትናንሽ ክፍሎችን ከቦ የነበረው ኃይልም በሠራዊታችን ታላቅ ጀግንነት ተደምስሰዋል ብለዋል። ከፍ ያለ ቁጥር ያለው የክልሉ ልዩ ኃይልና ሚሊሻ ምርኮኛ እየሆነ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።

መላው የኢትዮጲያ ህዝብ ለሰራዊቱ እያሳየ ያለው ድጋፍ ከፍ ያለ የሞራል ልእልና እንዳላበሰውም አስታውቀዋል። ለኢትዮጵያ ነቀርሳ የሆነው ይህን ከሀዲ ቡድን በመደምሰስ የሕግ የበላይነትና ህገመንግስታዊ  ስርዓት ለማረጋግጥ በብቃት እየተሰራ መሆኑን ኢፕድ ዘግቧል ።

የመከላከያ ኃይሉ ሕዝብ እንዳይጎዳ ለማድረግ ሕዝብ እና ጽንፈኛ ኃይሉን ለይቶ ለመምታት በጥንቃቄ እየተንቀሳቀሰ መሆኑንም ጄኔራል ብርሃኑ ተናግረዋል።

Please follow and like us:

By Eyasu Esayas

Entrepreneur, Writer, Business advocate and Teacher. Nice to have every soul on board. Eyasu do adore the HUMAN Nature. Join the Wonderful Team.

Leave a Reply

RSS
Follow by Email
Twitter
YouTube
Pinterest
LinkedIn
LinkedIn
Share
Instagram
Telegram
WhatsApp