አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በህወሃት ውስጥ ያለ ቡድን በአዲስ አበባ ከተማ ለጥፋት ተልዕኮ ያዘጋጃቸው የጦር መሳሪያዎች መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ገለጸ።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው እንደገለጹት፤ መዲናዋን ለማወክ ቡድኑ ያዘጋጀው ከ355 በላይ የተለያየ የጦር መሳሪያ ከ14 ሺህ በላይ ጥይቶች ጋር ተይዘዋል።

የጥፋት አጀንዳውን በማስፈጸም የተጠረጠሩ 162 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተካሄደባቸው እንደሆነም መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

የጥፋት ተልዕኮውን ለማስፈጸም የሚንቀሳቀሱ ሃይሎችን በቁጥጥር ስር ለማዋል ህብረተሰቡ ያደረገውን አስተዋጽኦ አድንቀው ምስጋና አቅርበዋል።

Please follow and like us:

By Eyasu Esayas

Entrepreneur, Writer, Business advocate and Teacher. Nice to have every soul on board. Eyasu do adore the HUMAN Nature. Join the Wonderful Team.

Leave a Reply

RSS
Follow by Email
Twitter
YouTube
Pinterest
LinkedIn
LinkedIn
Share
Instagram
Telegram
WhatsApp