የጉሌሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር አመራሮች፣ ሰራተኞች እና ነዋሪዎች ለመከላከያ ሰራዊት የደም ልገሳ መርኃግብር አካሄዱ፡፡
የደም ልገሳ መርኃግብሩ መከላከያ ሰራዊት ሀገርን ለመጠበቅ እያደረገ ያለውን ተጋድሎ ለመደገፍ ነው ተብሏል፡፡
በመርኃግብሩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ተፈራ ሞላ ኢትዮጵያ የብልፅግና ጉዞ እያደረገች ባለችበት ወቅት ጽንፈኛ ህወሓት የፈጸመው አስነዋሪ ተግባር መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በመሆኑም ከሀገር አልፎ ለቀጠናዊ ሰላም ሚናው የጎላ ለሆነው መከላከያ ሰራዊት ከጎኑ ለመሆናችን ማሳያ እንዲሆን ደም ለግሰናል ብለዋል፡፡
በጉሌሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አባወይ ዮሐንስ በበኩላቸው፣ “ደሜ ለሰራዊቴ፤ ህይወቱን ለሰጠኝ ደሜን እሰጣለው” በሚል መሪ ሐሳብ በክፍለ ከተማው የተከናወነው ተግባር ሁል ጊዜ ከሰራዊቱ ጎን መሆናችንን ለመግለጽ ነው ብለዋል፡፡
የክፍለ ከተማው ነዋሪዎች ከዚህ በኋላም በማንኛውም ሁኔታ ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡
አስተያየታቸውን ለዋልታ የሰጡ ደም ለጋሾች ጽንፈኛው ህወሓት የፈፀመውን ተግባር በማውገዝ ከመንግስት ጎን እንደሚቆሙ አረጋግጠዋል፡፡