ህወሓት መቀሌ በሚገኘው የሰሜን ዕዝ የመከላከያ ሠራዊት  ላይ ጥቃት መፈፀሙን አሜሪካ አስታወቀች።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፒዮ በትዊተር ገጻቸው ላይ እንደገለጹት፤  የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጪ ግንባር በትግራይ ክልል በሚገኘው የኢትዮጵያ መከላከያ ኃይል ሰፈሮች ላይ ጥቃቶችን ፈጽሟል።

የህወሓትን ጥቃት  ተከትሎ የተወሰደው እርምጃ እንዳሳሰባቸው ገልጸው፤ ሁኔታዎች በአፋጣኝ ወደነበሩበት እንዲመለስ ጠይቀዋል።

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ህወሓት በሰሜን እዝ የመከላከያ ሠራዊት ላይ ጥቃት መፈጸሙንና መንግስት ተገዶ ወደጦርነት መግባቱን መግለጻቸው ይታወሣል።

ህገመንግስቱን እና ህገ መንግስታዊ ስርአቱን ለመጠበቅ ሲባልም ትናንት የሚኒስትሮች ምክር ቤት በትግራይ ክልል ላይ ተፈጻሚ የሚሆንና ለስድስት ወራት የሚቆይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጁ ይታወሳል።

Please follow and like us:

By Eyasu Esayas

Entrepreneur, Writer, Business advocate and Teacher. Nice to have every soul on board. Eyasu do adore the HUMAN Nature. Join the Wonderful Team.

Leave a Reply

RSS
Follow by Email
Twitter
YouTube
Pinterest
LinkedIn
LinkedIn
Share
Instagram
Telegram
WhatsApp