አዲስ አበባ ፣ጥቅምት 26 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የመከላከያ ሰራዊት፣ የአማራ ክልል ልዩ ሃይልና ሚሊሻ አባላት ድል ማስመዝገባቸውን የአማራ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አቶ ተመሥገን ጥሩነህ ተናገሩ።

ርዕሰ መሥተዳድሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ እንደገለጹት የአማራ ክልል ልዩ ኃይል፣ ሚሊሻ እና የመከላከያ ሰራዊት በየደረጃው ያሉ ዓመራሮች እና አባላት በተቀናጀ መልኩ ያደረጉት ተጋድሎ ስኬታማ ነበር ነው ያሉት።

በትናንትናው ዕለት በሶሮቃ እና ቅራቅር ከዕኩለ ሌሊት እስከ ረፋድ ተደጋጋሚ ማጥቃት ተሰንዝሮ ነበር ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፣ ከረፋድ በኋላ በተሰነዘረው ማጥቃት በርካታ ቦታዎችን መቆጣጠር መቻሉን ገልጸዋል፡፡

“በተቆጣጠርናቸው ቦታዎች ያለው የህዝብ ድጋፍ ድንቅ ነበር፣ በርካታ ያለፍላጎቱ እንዲዋጋ የተገደደ የፀጥታ ኃይል በሰላም እጁን ሰጥቷልም” ብለዋል።

“እዋጋለሁ ብሎ የመረጠም ፊቱን አዙሮ እኛን ሲያግዝ ውሏል” ነው ያሉት።

“ጦርነት አንፈልግም ስንል ጠላታችን ድህነት ነው ከሚል እንጂ ጦርነት ካለማወቅ አይደለም ያሉት አቶ ተመስገን ዛሬም በሌላ ድል ታጅቦ ያልፋል” ብለዋል።

Please follow and like us:

By Eyasu Esayas

Entrepreneur, Writer, Business advocate and Teacher. Nice to have every soul on board. Eyasu do adore the HUMAN Nature. Join the Wonderful Team.

Leave a Reply

RSS
Follow by Email
Twitter
YouTube
Pinterest
LinkedIn
LinkedIn
Share
Instagram
Telegram
WhatsApp