አዲስ አበባ ፣ጥቅምት 25 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሰራዊቱ በሰፈረባቸዉ ካምፖች የተከፈተበትን የከሃዲዎች ጥቃት በብቃት መክቶ ወደ ጸረ ማጥቃት እርምጃ  መሸጋገሩን የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሰራዊቱ ተኩስ በተከፈተበት ካምፖች ሁሉ በጠንካራ መከላከል ውጊያ የከሃዲውን ሃይል በጀግንነት መክቶ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰበት ይገኛል፡፡

 የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊትና የአማራ የጸጥታ ሃይል ተቀናጅተዉ በሰሜን ጎንደር ዞን ቀራቅር በተባለ ቦታ የእብሪተኛዉ ቡድን የሰነዘረዉን የማጥቃት ውጊያ በብቃት በመመከት በዚህ ሃይል ላይ ከፍተኛ ሰብዓዊና ማቴሪያላዊ ኪሳራ አድርሶበታል፡፡ 

Advertisements
Advertisements
Advertisements

ሰራዊቱ በዛሬዉ እለት ከሰዓት በኋላ በወሰደዉ ቅንጅታዊ የማጥቃት እርምጃ ከቀራቅር በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘዉ ከፍተኛ ቦታ ላይ የነበረዉን የእብሪተኛዉ አጥፊ ቡድን ሃይል በከፍተኛ ሁኔታ በማጥቃት ቦታዉን ቁጥጥር ሥር ማዋሉን አስታውቋል። 

ጀግናዉ ሰራዊት በወሰደዉ የማጥቃት እርምጃ በዚህ ነብሰ በላ ቡድን ሃይል ላይ ከፍተኛ ሰብዓዊ ኪሳራ በማድረስ የቡድንና የነብስ ወከፍ መሳሪያዎችንም ማርኳል ፡፡

Please follow and like us:

By Eyasu Esayas

Entrepreneur, Writer, Business advocate and Teacher. Nice to have every soul on board. Eyasu do adore the HUMAN Nature. Join the Wonderful Team.

Leave a Reply

RSS
Follow by Email
Twitter
YouTube
Pinterest
LinkedIn
LinkedIn
Share
Instagram
Telegram
WhatsApp