በባሌ ሮቤ፣ ዶዶላና በለሎችም የኦሮሚያ አካባቢ በጽንፈኞች የተጠራው ሰልፍ የኢትዮጵያን ህዝብ እንዳጠፋ የአመሪካ ድምፅ ራድዮ ዘግቧል። እንደ ዘገባው ከሆነ ከአስር በላይ የሆኑ ሰዎች ሳይሞቱ እንዳልቀሩ ነው የተገለጸው።

በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልል የፀረ ሰላም ሃይሎች አደጋ እያስከተሉ እንደሆነ ይታወቃል። በተለያዩ የሃገርቱ ክፍል የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ህዝብረተሰብን በዘር ከፋፍሎ መግደል የተለመደ እየሆነ መጥቷል።

መንግስት የህዝብን ሰላም ለማስከበር እርምህምጃ መውሰድ እንደጀመረ ይታወቃል ይሁን እንጂ የገዥ ፓርቲ በውስጡ ሹክቻ ስላለበት ሁነታውን ማስተካከል አልተቻለም ።

የፌደራል ፖሊስ በትንላንትናው ዕለት በማንኛውም ሰልፎች ላይ እገዳ እንደጣለና፣ ይህንን ጥሶ አደባባይ የወጣ ካለ ህገወጥ እንደሆነ አስታውቆ ነበር። በህዝብ ላይ ሁከት በመቀቆስቀስ የተጠረጠረው አቶ ጃዋር መሃመድ ምፕታመሙን ለፍርድ ቤት ከመግለጹ ጋር ተያይዞ ለሁከት ቀስቃሾች የሰበብ መነሻ እንደሆነም ይታመናል።

በዛሬው ዕለት የደረሰውን አደጋ በተመለከተ ከመንግስት ባለስልጣናት የተሰጠ ምላሽ የለም። እንደ ዜና አውታሮቹ ከሆነ የፀረ ሰላም ሃይሎች እንቅስቃሴ ለማስቆም እንደተቻለ እየተዘገበ ነው።

Please follow and like us:

By Eyasu Esayas

Entrepreneur, Writer, Business advocate and Teacher. Nice to have every soul on board. Eyasu do adore the HUMAN Nature. Join the Wonderful Team.

Leave a Reply

RSS
Follow by Email
Twitter
YouTube
Pinterest
LinkedIn
LinkedIn
Share
Instagram
Telegram
WhatsApp