June, 22-2020

የወላይታ ዞን ም/ቤት 4ተኛ ዙር 7ተኛ የስራ ዘመን 2ተኛ አስቸኳይ ጉባኤ መርህ ግብር ላይ  በሰባት ነጥብ የተነሱ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ በሙሉ ድምጽ አጽደቀ።

Save on Orlando's Best Theme Parks!

የደቡብ ክልል ም/ቤት መፍረሱን ተከትሎ የሚነሱ ማንኛውም ጉዳዮች ሆነ በወላይታ ዞን ያለው አጠቃላይ እንቅስቃሴ ቀጥታ ከፌደራል መንግስት ጋር መሆን እንዳለበት የተነሱ ነጥቦች ያሳያል። እነዚህ ነጥቦች በዝርዝር ከሥር የተገለጹ ይሆናሉ።

  1. የወላይታ ህዝብ የጠየቀውን በክልል የመደራጀት ህገመንግስታዊ ጥያቄ ብቻ ነው። ከዚህ ውጭ የሚመጣ ማንኛውንም አይነት ምላሽ ሆነ ውሳኔ ም/ቤቱ የማይቀበል መሆኑና መንግስት የህዝባችንን ጥያቄ በአጭር ጊዜ ውስጥ ህገመንግስታዊ መንገድ ተከትሎ ህጋዊ ምላሽ እንድሰጥ፣
  2. የፌደረሽን ምክር ቤት በአጭር ጊዜ ውስጥ ህዝበ ውሳኔ እንዱያደራጅ ለምርጫ ቦርድ ውሳኔ ሰጥቶ እንድያስተላልፍ። ይህ ካልሆነ ግን ለሚፈጠረው ማንኛውንም አይነት ችግር ማዕከላዊ መንግስት ሃላፍነት መውሰድ እንዳለበት፣      (Shop Eye Care at Clearly)
  3. በደቡብ ክልል ምክር ቤት የህዝባችን ጥያቄ አልተመለሰም፣ ታፍኗል በሚል መልቀቂያ አስገብተው የመጡ ተወካዮቻችን ላይ የሚወሰድ የትኛውም ውሳኔ ተቀባይነት እንደሌለው እና የደቡብ ክልል ምክር ቤት ከአሁኑ በኋላ ተወካዮቻችን በሌሉበት ሁኔታ የወላይታ ህዝብን ሊወክሉ የሚችሉ አጀንዳዎች ጉዳዮችን ማየትም ሆነ ውሳኔ መስጠት እንደማይችል
  4. የሰላምና የፀጥታ ጉዳያችን ላይ የአካባቢያችን ፖሊስ፣ ሚልሻ ወጣቶችና የወላይታ ህዝብ በጋራ ክንድ ተባብሮ እንደሚሰራ እንድሁም አስፈላጊ በሆኑ ጉዳዮች የፌደራል ፖሊስ ከህዝባችን ጋር አብሮ እንድ ስር ነገር ግን የደቡብ ክልል ልዩ ሃይል ከአሁኑ በኋላ በአከባቢያችን የሰላምና የፀጥታ ጉዳይ እንደማይመለከተውና ከአካባቢያችን መውጣት እንዳለበ
    CarRental8 - Best Prices Guaranteed
  5. በክልል የመደራጀት ህገመንግስታዊ ጥያቄዎች በህዝብ ጥንካረ እና ትግል መመለሱ ስለማይቀር ምክር ቤቱ ልዩ ልዩ ኮሚዋችን በማደራጀት የቅድመ ዝግጅት ስራ መጀመር እንዳለበትና ይህን ስራ በበላይነት የሚመራ ጽ/ቤት እንድቋቋም

     ከጽ/ቤቱ ተግባራት በከፊል፣

  •የወላይታ ባንድራ ምን መሆን እንዳለበት

    • የወደፊቱ የወላይታ ክልላዊ መንግስት ህገ መንግስት ምን መሆን እንዳለበት የምለው ረቂቅ እንድዘጋጅ ፣ የሚቋቋመው ጽ/ቤት በእንደዚህ እና ተያያዥ ጉዳዮች በቀጣይ ወላይታን የሚመለከቱ ፖለቲካዊ ፣ ማህበራዊ እና እኮኖሚያዊ ጉዳዮችን በመተንተን ፖሊስዮችን እና ስትራተጂዎችን የሚያቀርብ እንድሆን ውሳኔዎችን አስተላልፈዋል።

6. አሁንም እንደ ቀድሞ ሁሉ የክልል ጥያቄያችንን ሰላማዊና ሰላማዊ መንገድን ብቻ በመከተል ትግል ማድረግ እንደሚገባ፣

7. ከጎረበት ህዝቦች ጋር ያለንን የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ማጠናከር እንደሚገባ እንዲምሁም የወላይታ ህዝብን ከወንድም ህዝቦች ጋር ለማጋጨት ድብቅ የፖለቲካ ሴራ አንግበው የሚንቀሳቀሱ ሀይሎች በማውገዝ በሙሉ ድምጽ የቀረቡ አጀንዳዎች ላይ ውሳኔ አስተላልፈዋል።

   የወላይታ ህዝብ የኢትዮጵያ ህገመንግስት ከጸደቀና ስራ ከዋለ ጀምሮ ትክክልነት ጥያቄ ሲያነሳ ቆይቷል። ይሁንና በህግ መንግስት አንቀጽ 47/2 ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች በማንኛውም ጊዜ የራሳቸውን ክልል የማቋቌም መብት እንዳላቸው የተደነገገ ብሆንም ይህ ህገመንግስታዊ መብት ተግባራዊ ሳይሆን እነሆ 27 አመታት ተቆጥረዋል። በነዚህ አመታት ይህ ህገመንግስታዊ መብት ተግባራዊ እንድሆን የወላይታ ህዝብ ታግሏል።መስዋዕትነት ከፍሏል።

በቀደምት አርበኞች እግር በመተካታችን፣ እኛ የዚህ ትውልድ አባላትም የአንድነት፣ የሰላም እና የሉዕላዊነታችን ፋና ወጊዎች ነን። እናቶቻችን እና አባቶቻችን የወሰኑት ታርካዊ ውሳኔ እና ለሰባት አመት ያደረጉት እልህ አስጨራሽ ጦርነት ለነጻነት፣ ራስን በራስ የማስተዳደር ሉዕላዊ ህዝብ ከምንም በላይ መሆናቸውን አሳይተውናል።

CarRental8 - Best Prices Guaranteed

   ይህ ጽሁፍ ቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የወላይታ ምክር ቤት አስቸኳይ ስብሰባውን እና የወቅታዊ አንገብጋቢ የቀድሞ የደቡብ ክልል መፍረስ ጋር ተያይዞ የተቀነጨበ ነው። ለትንታኔዎችና ዝርዝር ሁኔታዎች በድረ ገጻችን ላይ ማግኘት ይችላሉ።

  ኢያሱ ነኝ።

የወላይታ ም/ቤት አቋም መግለጫ
Please follow and like us:

By Eyasu Esayas

Entrepreneur, Writer, Business advocate and Teacher. Nice to have every soul on board. Eyasu do adore the HUMAN Nature. Join the Wonderful Team.

Leave a Reply

RSS
Follow by Email
Twitter
YouTube
Pinterest
LinkedIn
LinkedIn
Share
Instagram
Telegram
WhatsApp