አዲስ አበባ፣ህዳር 6፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮጵያ ብቻዋን የሕግ የበላይነትን የማስከበሩን ዘመቻ በብቃት ታጠናቅቃለች ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስታወቁ፡፡

የሐሰተኛው አጥፊ ቡድን መጨረሻ ተቃርቧል በማለትም ተናግረዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡

በተለይም ባለፉት ቀናት የታዩት ሁኔታዎች በህወሓት ውስጥ ያለውን አጥፊ ቡድን ትክክለኛ ማንነት የገለጡ ናቸው ሲሉም በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ ገልፀዋል።

የሕግ የበላይነትን በማስከበር እንዲሁም ኢትዮጵያን በመዝረፍና ሰላሟን በማወክ የተሠማሩትን ተጠያቂ በማድረግ፣ ለዘላቂ ሰላም  የሚሆን ጠንካራ መሠረት  እንገነባለን ነው ያሉት።

በዚህም በሰብአዊነት እና በሰላም ላይ ወንጀል የፈጸሙ ሁሉ ተጠያቂዎች እንደሚሆኑም ተናግረዋል፡፡

ፍትሕ እና የሕግ የበላይነትን ለማስከበር ባለን ውሳኔ በቆራጥነት እንገሠግሳለን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በልጆቿ  ጽናት እና ቆራጥነት፣ ኢትዮጵያ ብቻዋን የሕግ የበላይነትን የማስከበሩን ዘመቻ በብቃ ታጠናቅቃለች ብለዋል።

By Eyasu Esayas

Entrepreneur, Writer, Business advocate and Teacher. Nice to have every soul on board. Eyasu do adore the HUMAN Nature. Join the Wonderful Team.

How is that?

Discover more from Essu Center

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading