ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ሲሪል ራማፎሳ የኢትዮጵያ የሕግ የማስከበር ስራ ስለተገነዘቡ ምስጋና አቀረቡ

የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበርና የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ ኢትዮጵያ እያደረገችው ያለው  የሕግ የማስከበር ስራና በወንጀል የሚፈለጉ ሰዎችን ለሕግ ለማቅረብ እየተሰራ ያለውን ስራ በመገንዘባቸው ጠቅላይ ዐቢይ አህመድ ምስጋና አቅርበውላቸዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ምስጋናውን ያቀረቡት የወቅቱ የአፍሪካ ኅብረት ሊቀመንበር ሲሪል ራማፎሳ የላኳቸውን የቀድሞዋ የላይቤሪያ ፕሬዚዳንት ኤለን ጆንሰን-ሰርሊፍ፣ የቀድሞው የሞዛምቢክ ፕሬዚዳንት ጆአኪም ቺሳኖ እና የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ክጋሌማ ሞትላንቴ ያካተተ ልዩ መልእክተኞች በተቀበሉበት ወቅት ነው።

በውይይቱ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በትግራይ ክልል እያካሄደችው ስላለው የሕግ ማስከበር ዘመቻ ገለጻ አድርገዋል። 

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በዚሁ ወቅት ልዩ መልእክተኞቹ ኢትዮጵያ የበለጸገች እና የተረጋጋች እንድትሆን የማድረግ ተስፋ ሰንቀው ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሔ ማምጣት የሚለውን መርህ መሰረት አድርገው በመንቀሳቀሳቸው ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል፡፡

መንግሥት ከሁለት ዓመታት በላይ  ሕወሓት አገሪቱን ወደ አለመረጋጋት ለመክተት ሲያደርጋቸው የነበሩ ተግባራት ለረጅም ጊዜ በመታገስ እንዳሳለፈ ጠቅላይ ሚንስትር ጠቅሰዋል። 

የፌዴራል መንግሥት ሲፈጠሩ የነበሩ በርካታ ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ብዙ ጥረት ማድረጉን ጠቅሰው፣ በሰሜን እዝ በሚገኘው የአገር መከላከያ ሠራዊት ላይ የተፈጸመው የክህደት ጥቃትን ተክሎ  የአገሪቱን ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓት ለማስከበር የግድ  ሰራዊት እንዲንቀሳቀስ አድርገናል ብለዋል።

የፌዴራል መንግሥት በአገሪቱ ውስጥ በሚገኙ ክልሎች የሕግ የበላይነትን ማስከበር ሓላፊነቱ መሆኑንና ይህንን አለማድረግ ለአገሪቱ ህልውና አደገኛ የሆነ የአፈንጋጭነት ባሕል እንዲዳብር የሚያደርግ መሆኑን በአጽንኦት ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትግራይ ክልል እየተደረገ ባለው ሕግ የማስከበር ስራ የመከላከያ ሰራዊት በከተሞችና ሰዎች የሚበዙባቸው ቦታዎች ላይ ሰላማዊ ዜጎች ላይ ጉዳይ እንዳይደርስ በከፍተኛ ጥንቃቄ እየተሰራ መሆኑን ለመልዕክተኞቹ ገልጸዋል፡፡

በአካባቢው ለሚገኙ ዜጎች ሰብአዊ ድጋፍ  የሚያደርግ ከፌዴራል ተቋማት የተዋቀረ  ከፍተኛ ኮሚቴ መኖሩንም  ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ተናግረዋል፡፡

በጦርነቱ ምክንያት የተፈናቀሉ ዜጎች ከዚህ ከቀደም ወደነበሩበት ቦታ ከመመለሳቸው በፊት የሚቆዩባቸው አራት የመጠለያ ጣቢያዎች መዘጋጀቱንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡

የህወሃት ጁንታ እና በማይካድራ በዜጎች ላይ ጭፍጨፋ የፈጸሙ የህወሃት ተላላኪዎችን ለፍርድ ለማቅረብ መንግስት እየሰራ እንደሆነም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለመልዕክተኞቹ ገለጻ አድርገዋል፡፡

የአንድ የቡድን የበላይነት ወይም የሌላ ቡድን ጭቆና እንዳይኖር ሁሉን አቀፍ ዴሞክራሲ ስርዓት በአገሪቱ እንደሚገነባም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገልጸዋል፡፡

   Https://Ethiopianshow.com

Entrepreneur, Writer, Business advocate and Teacher. Nice to have every soul on board. Eyasu do adore the HUMAN Nature. Join the Wonderful Team.

Related Posts

Bidding Farewell to Halifax's Flower Market: Exploring the Significance of Nature in Art

Say Goodbye to Halifax’s Flower Market: Discovering the Beauty of Nature in Art!

“Say Goodbye to Halifax’s Flower Market: Discovering the Beauty of Nature in Art!” The Halifax Flower Market has been a beloved part of the city for over…

Can a Web browser be swift, user-friendly, and profitable at once? Definitely yes, if it’s the new CryptoTab Browser

Can a Web browser be swift, user-friendly, and profitable at once? Definitely yes, if it’s the new CryptoTab Browser. Advanced software like this can be both a…

Earn BTC

It’s so simple to earn BTC nowadays! Until recently, you had to invest or buy enormous and expensive hardware. But for now, it has changed, and I…

You know what we are harvesting?- It is just a coin

Honey, Money and Bitcoin to your wallet when you reimagin Crypto trading ecosystem Honey and Money are my most favorite Love finders. Bitcoin is really a game…

What is your question?

Earn Bitcoin and do your business? Yes! Earn Bitcoin and spend time with family? For sure! Earn Bitcoin and have fun? That’s right! It all became a…

Wanna mine some bitcoin

Wanna mine some bitcoin, but have no farm? Now you don’t need it! Just install CryptoTab, the world’s first browser with built-in mining features. Fast, convenient and…

Say Something