የወላይታ ህዝብ ክልል ከመሆን ጋር በተያያዘ እና በህገ መንግስት አግባብ በተጠየቀው ፣ የመንግስት ምላሽ እስርና ግድያ መሆኑ ብዙዎችን አስቆጥቷል። በሃገርቷ ውስጥ ለምከሰቱ ጥፋቶች የመንግስት እጅ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋርእንዳለበት ይታመናል።
መንግስት ባመነው እንኳን ከ700 በላይ የብልፅግና አባላት፣ በወንጀል ተጠርጥረው በህዝምግ ስር ይገኛሉ።
በለውጥ ተመካሽቶ፣ ሳምንት ሳይቆይ ጦር ለማዝመት እየፎከረ የቆየው የዶክተር አብይ አህመድ ብልፅግና ፓርቲ ህዝብ ላይ አደጋ አስከትሏል። የውሳኔ ሰጭነት እና በዘር ላይ የተመሰረተ አመለካከት እንደምያጠቃው እየተነገረ ያለው የለውጥ መሪ ተቃዋሚ ፖርቲዎችን በሙሉ ማለት በሚችል ደረጃ አስሯቸዋል።
የጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ የፖለቲካ አመለካከት ከሚድያ ግብአት ውጪ ምንም ፋይዳ የለውም በማለት በሃገርቷ ውስጥ ረብሻ ተቀስቅሷል።
የደቡብ ክልል ተብሎ ይጠራ የነበረው የቀድሞ ክልላዊ አስተዳደር ከፈረሰ ወዲህ በሃገርቱ ከባድ ውዝግብ አስከትሏል።
መንግስት ለተፈጠሩ አደጋ ሁሉ ሃላፊነቱን እንዲወስድና በግፍ የታሰሩት እንድፈቱ በከፍተኛ ተቃውሞ ጫና እየተደረገ ይገኛል ። በመልካም አስተዳደር እጦትና በዘር የተከፋፈለችው ኢትዮጵያ ፣ ዛሬም የወጣቶችን ህይወት በጥይት እሳት እያለች ትገኛለች።
ማእከላዊ መንግስት በዘረኝነት እና በሆድ አደር ግድየለሽነት ብቻ ሳይሆን የተደበቁ ሴራዎች ሊኖሩ እንችሉም ከባድ ጥርጣሬ አለ። ይህንን ለሣላሳ አመት አከባቢ የበሰበሰውን መጥፎ አመለካከትና የፖለቲካ አፈና ማስቆም የዘጎች ዋስትና መሆኑ ጥርጥር የለውም።
የዘጎችን ድምፅ ማፈን ከአደጋ በስተቀር ፋይዳ የለውምና መንግስት በአስቸኳይ ጠመንጃ አስቀምጦ ህዝብን ማዳማጥ እንድጀምር እንጠይቃለን።
Prepared by: Eyasu Esayas
- The Thrilling Powerhouse: Unveiling the 2023 Models’ Unmatched Performance and Driving Prowess
- Fairview Car Dealers: Your Gateway to Dream Cars in Fredericton, NB
- Fairview Car Dealers in Fredericton, NB: Driving Excellence in Automotive Services
- The Enigmatic Beauty of Love Blogger: A Birthday Celebration”
- Advanced Infotainment Systems: How Hyundai Models Redefined In-Car Entertainment