የትግራይ ልዩ ኃይል አባላት ከመከላከያ ሰራዊት ጎን እንዲሰለፉ ጥሪ ቀረበ
የጽንፈኛው የህወሓት ቡድን መሪዎች ቤተሰቦቻቸውን ወደ ሌላ ሀገር በማሸሽ የትግራይ ልዩ ኃይልን ወደ ጦርነት በማሰለፍ እያደረገ ያለው የሞት ሽረት ትግል ተገቢ ባለመሆኑ ከመከላከያ ጎን እንዲሰላፍ የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ትዴፓ) ጥሪ አቀረበ፡፡
ልዩ ኃይሉ አንድነቱን አጠናክሮ ከመንግስት ጎን መሰለፍ እንዳለበትም መልእክት አስተላልፈዋል፡፡
ህገ-መንግስቱን መጣስ ሀገርን መካድ መሆኑንም ትዴፓ ዛሬ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል፡፡
በሀገሪቱ የተደረገው ስር ነቀል ለውጥን ለመቋቋም ሸሽቶ ከተቀመጠው ቡድን የሞት ሽረት እያደረገ እንደሚገኝ የትዴፓ ሊቀ መንበር ዶ/ር አረጋዊ በርሄ ተናግረዋል፡፡
ዶ/ር አረጋዊ የመከላከያ ሰራዊቱ እነዚህን ፀረ ሰላም፣ ፀረ አንድነት፣ ፀረ ህዝብ የሆኑ ቡድኖች ሳይደመሰስ ወደ ኋላ እንደማይመለስ እምነት አለኝም ብለዋል፡፡
(በስመኝ ፈለቀ)