የስዳማ ህዝብ ጨካኙን አውሬ፣ ከሃዲ ጁንታ የህወሃት አሸባሪ ቡድን በቃችሁ ብለዋል።
የሃገራችንን ኢትዮጵያ ሰላም በደማችን ዋጋ እናመጣለን፣ የጠላትም ክንድ እንሰብራለን ብለዋል።
የጽንፈኛው የህወሓት ቡድን በሰሜን እዝ መከላከያ ሰራዊት ላይ የሰነዘረውን ጥቃት ተከትሎ መንግስት የማያዳግም እርምጃ በመውሰድ የሕግ የበላይነትን እያስከበረ ይገኛል፡፡
የጁንታው ቡድን እየተወሰደበት ባለው እርምጃ በተስፋ መቁረጥ ውስጥ ሆኖ የንጹሐንን ሕይወት እየቀጠፈ መሆኑ ይታወቃል፡፡

የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ጁንታውን ድባቅ መትቶ ወንጀለኞችን ለሕግ ለማቅረብ እያደረገ ያለውን ተጋድሎ ሕዝቡ ደም በመለገስ፣ የዓይነትና የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ አጋርነቱን እያረጋገጠ ይገኛል፡፡
. ለመሆኑ ይህ ሕዝባዊ ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል እርስዎ ምን አስተዋጽኦ እያበረከቱ ነው?

. የጽንፈኛውን ቡድን ዓላማ ለማስፈፀም የሚንቀሳቀሱ ግለሰቦች ሊፈጥሩት የሚችሉትን ጥቃት ለመከላከል እንዲቻል ሕብረሰተሰቡ ከጸጥታ አካላት ጋር በመሆን የአካባቢውን ሰላምና መረጋጋት እንዲያስጠብቅ ምን ሚና ሊኖረው ይገባል ይላሉ?
አብራችሁን ስለሆናችሁ ደስተኞች ነን!