የህወሓት ቡድን የሀገር መከላከያ ጦር ጄት መትቼ ጥያለሁ ሲል የገለጸው ፍጹም ሀሰት ነው – ሜጀር ጄኔራል መሐመድ ተሰማ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 30፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጽንፈኛው የህወሓት ቡድን የሀገር መከላከያ ጦር ጄት መትቼ ጥያለሁ ሲል የገለጸው ፍጹም ሀሰት መሆኑን የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ኢንዶክትሪኔሽን ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጄኔራል መሐመድ ተሰማ ተናገሩ።

አየር ሀይሉ አሁንም ቢሆን የተመረጡ ቦታዎችን ማጥቃቱን አጠናክሮ ቀጥሏል ነው ያሉት።

የጥፋት ቡድኑ በመከላከያ ሃይል እየደረሰበት ባለው ጥቃት በርካታ ይዞታዎችን እየለቀቀ መሆኑን የገለጹት ሜጀር ጄኔራል መሐመድ፤ በርካታ የክልሉ ልዩ ሃይልና ሚሊሻዎችም በሰላም እጃቸውን እየሰጡ ይገኛሉ ብለዋል።

Say Something