ክቡር አቶ አገኘሁ ተሻገር የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ሆነው ተሾሙ፡፡

የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን ጥሩነህ የስልጣን መልቀቂያ ጥያቄ ለክልሉ ምክር ቤት አቀረቡ

ባሕር ዳር፡ ጥቅምት 29/2013 ዓ.ም (አብመድ) ርእሰ መሥተዳደር ተመስገን ጥሩነህ ለሌላ ኃላፊነት መታጨታቸውን ተከትሎ ለክልሉ ምክር ቤት ያቀረቡትን ጥያቄ በመቀበል በምትካቸው የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ በእጩነት ያቀረባቸው በምክትል ርእሰ መስተዳድር ማዕረግ የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ የነበሩት አቶ አገኘው ተሻገር የክልሉ ርእሰ መስተዳድር ሆነው ተሹመዋል፡፡

የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን ጥሩነህ የስልጣን መልቀቂያ ጥያቄያቸውን ያቀረቡት ምክር ቤቱ 5ኛ ዙር 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 16ኛ መደበኛ ጉባኤውን በሚያካሂድበት ወቅት ነው።
ሀገሪቱ ካለችበት ወቅታዊ ሁኔታ አንፃር በተሠጣቸው ተልእኮ ምክንያት ጥያቄውን ያቀረቡት ርእሰ መስተዳድሩ ፓርቲያቸው በተሠለፈበት ሀገርን የማዳን ስራ ላይ የሚጠበቅባቸውን ለማበርከት ስምሪቱን መቀበላቸውን ለምክር ቤት አባላት ገልፀዋል።
ክልሉን በአስቸጋሪ ወቅት የተረከቡት ርእሰ መስተዳድር ተመስገን ጥሩነህ የስልጣን መልቀቂያቸውን አስመልክቶ የምክር ቤት አባላቱ በጉዳዩ ላይ ካካሄዱት ሠፊ ምክክር በኋላ ጥያቄያቸውን ተቀብሏል።
ምክር ቤቱም ለቀጣይ የክልሉ ርእሰ መስተዳድርነት አቶ አገኘሁ ተሻገር በእጩነት አቅርቧል።

Say Something