ሰሞኑን ዐረብ ሃገር ካሉ ሴት እህቶቻችን የምንሰማው ድምጽ ያሳዝናል። ሠርቶ ሃገርንና ህዝብን ለመርዳት የሄዱ ወርቃማ ወገኖቻችን ችግር ውስጥ ናቸው። እርግጥ ይህ መከራና ስቃይ በእናት ሃገር ኢትዮጵያ ከተጀመረ የሰነበተ ብሆንም ባለን አቅም ሁሉ ስንታገል ቆይተናል። እነዚህ ወገኖቻችን በበሩትና ዱባይ ለገጠማቸው አሳዛኝ ጦስ ውስጥ: አስቸኳይ መፍትሄ ያስፈልገዋል።

በተለይ በበሩት ያሉ ኢትዮጵያውያን በአሁኑ ሰዓት መዳ ላይ ወድቆ ይገኛሉ። ምግብና ውሃ በማጣት ለአዳጋች የህይወት ፈተና ገጥሟቸው ይገኛል። በሊባኖስ ያለው የፖለቴካ ቀውስ ተከትሎ የተናወጠችው ያች አረብ ሃገር፣ ዛሬ ደግሞ ኮሮና መጣባት። ሁሉንም ሰበብ ተጠቅመው ጭካንያቸውን በአደባባይ ስያሳዩ ቆይተዋል። የኮሮና አደጋ ባስከተለው አሳዛኝ ጦስ ውስጥ እንገኛለን።

ወይዘሮ ሃገር እንደገለጹት ከሆነ የበሩት ቆንሥላ ወይንም እምባሲ ተወካይ አሳፋሪ እንደሆኑ አረጋግጣለች። ለመሥሪያ በታቸው ሥም እንኳን ስንል እህቶቻችንን ሃገር ቤት መመለስ ነበር ህጉ።

አቶ ማን ፍጣሞ የተባሉ የቆንሥላ አሥተዳደር ልበለው ተወካይ ሃይ ልባሉ ይገባል። ዛሬ ላይ የደረሰብን ዐደጋ ከፍተኛ ከመሆኑም በላይ በሃገር ደረጃ ውርደት ነው። ይህን ተገንዝበው አስፈላጊ ሁሉ ድጋፍ እንዲያቀርብ ዕናስገድዳለን። የሃገር ግዴታ ለመወጣት ካልቻሉ ዕንድታወቅ ዕንፈልጋለን።

በደረሰን አሳዝኝ የዕኮኖምና ማህበራዊ ጉዳዮች ተያይዞ ብዙ ዐጭበርባርም ተነስቷል። ባለን ዐቅም ሁሉ ተብብረን ህዝባችንን መርዳት ግድ ይላል።
ዛሬ ለእቶቻችን በተቸገሩበጥ ሰእት ለመድረስ ዕየሮጥን ዕያለ ‘ጎ ፋንድ’ Go fund በምንለው ዘመናዊ መረዳጃ ብዙዎች ተነሥተዋል። ይህንን ተከትሎ እርዳታ የሚያሥፈልኃቸው እህቶቻችን ስቃይ ላይ ናቸው።

ኢትዮጵያዊያን በአንድ ልቦና ተንስተው፣ በጋራ ማለፍ ያለብንን እንስራ ። ይህ ዘመን ከባድ ነው። የሃገር ውስጥ ፓለቲካ ጡዘት ሳይበርድ ኮንሮና መጥቶብናል። አሁን ጊዜው ግን በጋራ መረዳዳት ያለብን ወሣኝ የህልውና ዕዳ ነው። በ ጎ ፋንድ በኩልም ብሆን መርዳት ያስፈልጋል። እውነተኛ መገናኛውችን ጊዜው ስደርሥ የማሣውቅ ይሆናል።

በሩትም ሆነ በመካከለኛው ምስራቅ ያለው የውጭ ጉዳይ መስርያ ቤት ዕርዳ ማድረግ ያስፈልጋል።

የኢትዮጵያ መንግስት በዚህ ጉዳይ አስቸኳይ ምላሽ ዕንድያደርግ የሁሉም ኢትዮጵያዊያን ጥሪ ነው። ወደ ፖለቲካው እንመለሳለን፣ ሃገር ለመታደግ መጀመሪያ መሥራት አለብን።

የኢትዮጵያ አምላክ ይጠብቀን።

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኖራለች።

Contact me|: Email: essotimes@yahoo.com                                                                                       Tel-no. +15063047077                                                                                I am Eyasu 

By Eyasu Esayas

Entrepreneur, Writer, Business advocate and Teacher. Nice to have every soul on board. Eyasu do adore the HUMAN Nature. Join the Wonderful Team.

How is that?

Discover more from Essu Center

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading