ምን ይሁን ውጤቱ፣ የት ይሁን የጀመርነው? የእውነት እየሞትን በውሸት መተላለቅ እስከ መቼ ይወስደናል?
ለዘመናት በአንድነትና በህብረት የኖረውን ህዝብ በፖለቲካ ድራማ ለሞት መጋበዝ የሰው ልጅ ህልም አይደለም። ይህ በገበያ ላይ የዋለ የጦርነት አዋጅ ለማንም የሰው ልጅ አይበጅም።
የህዝብ አንጡራ ሃብት የሆነውን የጋራ ኑሮ በግለሰቦች ፍላጎት ማፈን ለሁሉም የሰው ዘር አይበጅም። አዲስ አበባ አውድሞ ፣ ማንም ንው ዮርክ (NEW YORK) ውስጥ በሰላም ለመኖር ማሰብ የሆድ እዳሪ እንጂ ፋይዳ የለውም። የሰው ልጅ በተፈጥሮ የታሰረ የማህበራዊ ኑሮ ውጤት ነው።
የዛሬው የኢትዮጵያ መንግስት አስተዳደራዊ ይዘት ከመነሻው ይልቅ መድረሻው ያሳስበኛል።
ሰው በተፈጥሮ #ኢትዮጵያ እንደሆነ ለማመን ጊዜ አይፈጅም። ዛሬ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ አንድ ሆኖ እያለ የውጭውን ትዕዛዝ የተቀበሉ ባንዳዎች በገዛ እናታቸው ላይ ጨክነው ማየት ያማል።
ጦርነት አማራጭ አይሆንም፣ ነገር ግን ጠላት እየፎከረ መለመን የኢትዮጵያ ህዝብ ባህል አይደለም። ነገር ጠላት ማነው?
ጠላት ማነው?
ጠላትን መፈለግ ጠላት እንዳልተፈጠረ ያሳያልና፣ ጠላት ሞልቶ ምርጫ ውስጥ አንገባም። እርግጥ ከጠላት የተሻለ አይመረጥም። የጊዜ ጉዳይ ነውና፣ በባህላዊ አባባል “የጠላት ጠላት ወዳጅ ነው’ ፣ ዛሬ ላይ አይሰራም። መቼም የወንድሜ ግጭት ጠላት አያደርግምና ጠላት ማነው?
እኔ፣ ኢትዮጵያዊ ጀግና ነኝ። ” ጀግና” ያልኩት ኢትዮጵያዊ በመሆን ብቻ ነው። ይህንን እውነት እና ጀግንነት ያስረከቡኝ የኢትዮጵያ ሰማዕታት ለዘላለም በክብር ይኑሩ። ዛሬ፣ የጊዜ ጉዳይ ነውና ህይወት የታርክ ውጤት ሁኖ መጥቷል።
ውጊያ መፍትሄ ባይሆንም ለመፍትሄ መነሻ ይሆናል። ለመዋጋት ጠላትን ማወቅ ግድ ይላል። ጦርነት የማይቀር ከሆነ በእምፔሪያሎች ቅኝት ባይሆን ይመረጣል። እንግዲህ የጋራ ጠላት ከታሪካዊ ጦስ ‘ግብፅ’ ጋር በመሆን ለሁሉም ኢትዮጵያ ህዝብ እልቂት ተመኝተዋል። የትኛውም ቡድን ኢትዮጵያ ውስጥ ውጊያ ካማረው ጥርቅም አመሪካ (U.S.A ) እና ግብፅ( Egypt) ወዳጅ ሁኖ ይነሳል። እንግዲህ በክፍያ እምዬ ኢትዮጵያ መስዋዕት መሆን አለባት? ያማል!
እምፕሪያሎች ሁለቱንም ተዋግዎች ደግፈው በማዋጋት የተካኑ ናቸው። በዋናነት ግብፅ ለ 50 አመት የሰራችው የኢትዮጵያን እልቂት ተግባራዊ እንዲሆን አንፈልግም።
አማራጭ ፣ ለእውነት መዋጋት ብቻ ነው። እርግጥ በኢትዮጵያ እናት አብራክ ውስጥ ጠላት የለም። ባንዳ አለ። ባንዳ እያለ ቁጣ አይቆምም።
ቁጣ ጦርነት አይደለምና በፍቅር ለመኖር ህግን በቁጣ ማስከበር ግድ ይላል።
ህግ እና የህግ ስርዓት ድርድር አያስፈልግም። የሰላም ጅማሮ የጦርነት ጫፍ አይደለም። መዳረሻው የሰላም ቆራጥ “የሰላም ታጋይ” በመሆን ነው።
በወገኖቻችን እየተቆጣን፣ ጠላትን እንዋጋለን።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ።
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር።