በኢትዮጵያ መሰረታዊ ጉዳይ ላይ እንደ ህዝብ መስራት የህልውና ግዴታ እንደሆነ ጥቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ የተረዱ ይመስለኛል።

ስም ማንሳት አይቀርምና ይነሳል። ‘ዐብቹ’ እሽሩሩ ያልነው የአንድ ወቅት ወረት ሆኖ ዕንደማይቀር እርግጠኛ ነኝ። ድካም ያለበት ከባድ አደራ በእጅዎ ይገኛል።ብርታት የእግዚአብሔር ነውና ለእርስዎና ለሃገራችን ብርታት ይሁን።

Prime minister Abiy Ahmed

በአሁኑ ጊዜ እንኳን የይድረሱልን ጥሪ እንደ ቡራዮ ዐልተሰማኝም እንዳይሉን። እርግጥ መስማት አለመቻል ድክመት ላይሆን ይችላል። ከሰሙ በሃላ ግን ምን አደረጉ ነው ጥያቄው። ትልቅ ስም በአለም በመያዝ የተሸለሙ ጠቅላይ ክብርና ማዕረግ ጥሩ ነበር። የያኔውን ጭብጨባ ዛሬም እጠብቃለሁ። መጠበቅ ሆኖ ቀረ እንጂ። እንኴን ጭብጨባ ጩሄት መጣብን። ዋይታ ሆነ። ዛሬም ተስፋ አንቆርጥም። ለውጥ እንጠብቃለን። ህዝብ ይመርጣል። ምርጫ የሚባል መብት አለ። እነሆ ንጉስ ለመሾም ሳይሆን ምርጫ እንጠብቃለን።

የውሳነው መጨረሻ በህዝብ እጅ ነው። ውሳኔ የህዝብ ካልን ለህዝብ ምርጫ እነጂ የእነ አብይ ቅባት አይደለም። ቅባት ይዘው ለማንገስ ከሆነ ሩጫው፣ ትዝብት ነው ትርፉ።

ዘመን አለፈና ኮሮና ስመጣ ነገር ተለወጠ። ለውጥ እንዳማረን ለውጥ ያሰብነው ምርጫ ይሄው ተቃርቧል።

ወ/ት ብርቱካን ምደቅሳ የምርጫውን ቀመር የሙጥኝ ብለውታል። መቼም አንዳንድ ፓለቲከኛ ዘመን ተሻጋሪ አገኘን ብለውን ነበር። እርግጥ ስናጨበጭብ ሁሉ ትዝ አለኝ።

በጥሩ ዘመን ብርቱካንን አቅፈን አብረን ደለቅን። ምነው ዛሬ ያ የያኔው ንግስና ዘመን ነው ብለው የዘመሩት መዝሙር ተቀይሯል? ጥያቄ አለኝ።

የውሳነው መጨረሻ በህዝብ እጅ ነው። ውሳኔ የህዝብ ካልን ለህዝብ ምርጫ እነጂ የእነ አብይ ቅባት አይደለም። ቅባት ይዘው ለማንገስ ከሆነ ሩጫው፣ ትዝብት ነው ትርፉ።

ደቡብ በምል ስያሜ እየተጠራ ያለው ክልል የህዝብ ጥያቄ መሆኑ በተረሳበት ሰዓት፣ እስክስታ ማውረድ ትዝብት ነው። በህግ ቃላት ለማሽሞንሞን ዳላስ ላይ የቀመረ፣ ረመጥ እንጂ መሰረት የለውም።ይህ ሁሉ በሃገር ላይ የተደቀነው አደጋ በግልጽ ያሳያል። በአእምሮ በሳል ወ/ት ብርቱካን ታርክ የምወቅሳቸውን ስራ እንደማይሠምሰሩ ለማመን ግዜ ልወስድብኝ ይችላል።

በገጠመን አንገብጋብ ጦስ አልፈን ለመገኘትና ሃገር ለማዳን መተባበር የተሻለ ይመስለኛል። የህዝብ መሠረት እንዳይናጋ ከመስራት አንጻር ወሳኝ ስራ ይጠበቃል። ተቋማት በሙሉ በሃገር ህልውና ላይ ትኩረት በማድረግ መስራት አማራጭ የለሌው ሁናቴ ነው። የወገን ጥር እና ጩሄት በወድያ በኩል እየበረከት ዝምታ መምረጥ ያሥነውራል።

አረብ ሃገር በምኖሩ ኢትዮጵያዊያን እህቶቻችን ላይ የምደርሱ አደጋ ከባድ ነው። ሃገርን ለማዋረድ በተለያዩ አቅጣጫ የኢትዮጵያ ፀር የሆኑ አመለካከቶች እየበረከቱ መጥተዋል።

ግብጽ የሃገራችንን አንድነት ለማዳከም የምትሄደው አቅጣጫ አደጋ አለው። በኑሮና በእኮኖሚ የተጎዳውን ህብረተሠባችንን ለከፋ ጉዳት ለማድረስ እያሰሩ ይገኛሉ።

በአሁኑ ሰዓት እጅ ለጅ ተያይዘን መስራት ይጠበቅብናል። እጅ ለእጅ ያልኩት የአካል መያያዝ ሳይሆን የሃሣብ ጽኑ፣ የሃገር አንድነት መሆን አለበት።

ጠቅላይ ሚንስትር አብይ : ይህንን ጊዜ ታሳቢ አድርገው ብርታት እንድያሳዩ እንጠይቃለን። ስራ ክቡር ነው። የእርስዎ መስሪያ ቤት ስራ ይስራ። በበሩት ከተማ ሊባኖስ ላሉት ወገኖቻችን ይድረሱላቸው። ዘመን ይሄዳል።ዘመን ያልፋል። ይህም ያልፋል። ንጉስ ይወለዳል ይሞታል። በሚያልፍ ዘመን የማያፍ ፎቶ ሳይሆን ታርክ ሰርቶ ማለፍ ጥሩ ነው። ጠብብ በጥበቡ ጊዜውን ይዋጃል- እንግዲያውስ ይሄው።

ኢያሱ ነኝ።

Essotimes@yahoo.com

Say Something