በኒዮርክ የሚኒተሪ አታሸ ሆነው ሲሰሩ የነበሩት ሜጀር ጄኔራል ፍስሀ ኪዳኑ ከሓላፊነት ተነሱ

በኒዮርክ የሚኒተሪ አታሸ  ሆነው ሲሰሩ የነበሩት ሜጀር ጄኔራል ፍስሀ ኪዳኑ ከሓላፊነት ተነሱ

~~~~~

በኒውዮርክ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጽ/ቤት የሚኒስትሪ አታሽ ሆነው ሲሰሩ የነበሩት ሜጀር ጀኔራል ፍስሀ ኪዳኔ ከኃላፊነት ተነስተዋል።

ጀኔራሉ ከሐላፊነት እንደተነሱ በሀገር መከላከያ ሚኒስትር በኩል ደብዳቤ እንደደረሳቸው በአሜሪካ ጥገኝነት መጠየቃቸውም ታውቋል።

ሜጀር ጄኔራሉ ፍስሀ ኪዳኔ በሐገር መከላከያ ሰራዊት የምዕራብ እዝ ኃላፊ ሆነው ሰርተዋል።

የምዕራብ እዝ ኃላፊ በነበሩበት ወቅት በሰሜን ጎንደር ጭልጋና መተማ አካባቢ ከሱር ኮንስትራክሽን ጋር በመተባበር የቅማንትና የአማራ ህዝቦችን ግጭቶች በበላይነት መርተዋል።

ሜጀር ጀኔራል ፍስሀ ኪዳኔ በሁለቱ ህዝቦች መካከል ግጭት እንዲፈጠር ከመምራት በተጨማሪ በወቅቱ በቦታው የተሰማራውን የመከላከያ ሰራዊት ከተልዕኮው ውጭ በመስጠት ላስፈጸሙት የሰባዊ መብት ጥሰቶች በህግ ተጠያቂ ሊሆኑ ይገባል።

አሁንም ከተሰጣቸው ሐገራዊ ተልዕኮ በማፈንገጥ በተለያዩ አለም ሀገራት ከሚገኙ ኤምባሲዎች ጋር በሚስጢር በመገናኘት የወንጀለኛው ትህነግን ተልዕኮ ሲያስፈጽሙ መቆየታቸው ታውቃል።

በሌላ በኩል የኢትዮጵያ መንግሥት በተለያዩ የዓለም ሀገራት የኤምባሲ አመራር ሆነው በሃላፊነት የሚሰሩ አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ መውሰዱን ይቀጥላል ሲሉ አንድ የውጭ ጉዳይ ሚነስትር ከፍተኛ ባለስልጣን ገልፀዋል።

Say Something