በሕወሃት ውስጥ ያለው ወንጀለኛ ቡድን ፍርሃትን ለመንዛት እና የሽብር ጥቃትን ለማድረስ አስፈፃሚ መረብ ማቋቋሙ ተገለፀ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 3 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሕወሓት ውስጥ ያለው ወንጀለኛ ቡድን በአዲስ አበባ እና በሌሎች የሃገሪቱ ክፍሎች ፍርሃትን ለመንዛት እና የሽብር ጥቃትን ለማድረስ አስፈፃሚ መረብ ማቋቋሙን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈፃፀም መርማሪ ቦርድ አስታወቀ፡፡

የኢፌዴሪ መንግሥት በትግራይ ክልል የሚያካሂደውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እና የሕግ ማስከበር ኦፕሬሽን መረጃ ማጣሪያ እንዳስታወቀው ግጭቶችን ለማነሳሳት እና በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የሽብር ጥቃቶችን ለማካሄድ ተልዕኮ ከሕወሓት ወስደው በመንቀሳቀስ ላይ ናቸው ተብለው የተጠረጠሩ ግለሰቦች በፌደራል እና በአዲስ አበባ ፖሊስ በቁጥጥር ስር እየዋሉ ነው፡፡

ተጠርጣሪዎቹ ከተለያዩ የኑሮ ሁኔታ እና የሙያ መስክ የተውጣጡ፣ የተለያዩ ብሔር ተወላጆች መሆናቸውን አስታውቋል፡፡ 

በቁጥጥር ስር የዋሉት ተጠርጣሪዎች ጠቅላላ ቁጥር ወደ 150 አካባቢ ሲሆን ከእነዚህ ተጠርጣሪዎች መካከል ጥቂቶቹ የሚደቅኑት የፀጥታ ስጋትን አነስተኛ መሆኑን ከግምት ውስጥ በማስገባት በዋስ ተለቀዋል፡፡ 

አንዳንድ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች እና ግለሰቦች በተሳሳተ መንገድ የተጠርጣሪዎቹን ቁጥር ያልተረጋገጠ እና የተጋነነ መረጃ እያሰራጩ የሚገኙ ሲሆን የሕግ አስከባሪው አካል አሠራርና ደንብን የተከተለ እንጂ እንደሚወራው በማንነት ላይ ተመስርቶ ግለሰቦችን የሚያጠቃ አይደለምም ነው ያለው፡፡

ሁሉም ዓለም አቀፍ አጋሮች እና ተዋንያን በሕወሓት የጥፋት ቡድን እየተፈፀመ ያለውን የውሸት የመረጃ ዘመቻ ልብ እንዲሉ ጥሪ እናቀርባለንም ብሏል።

Say Something