ሠራዊታችን ሀገርን ከጥፋት የማዳን ተልዕኮውን በአጭር ጊዜ ውስጥ ያጠናቅቃል – ሜ/ጄ መሀመድ ተሰማ

ሠራዊታችን ሀገርን ከጥፋት የማዳን ተልዕኮውን በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደሚያጠናቅቅ የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽን ዋና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሜጀር ጄነራል መሀመድ ተሰማ አስታውቀዋል።

ሜ/ጀ መሀመድ ተሰማ የኢትዮጵያን ዕድገት የማይፈልጉ ታሪካዊ ጠላቶች የህዳሴ ግድባችንን እንዳያደናቅፉ የሀገራችን የፀጥታ ሀይሎች በተጠንቀቅ በቆሙበት ባሁኑ ሰዓት፣ የናት ጡት ነካሾች ሀገራችንን በመድፈር ውጊያ ከፍተውብናል ብለዋል።

ይህ ጦርነት ሀገርን ለውጭ አሳልፎ የሚሰጥና ፅንፈኛው ሀይል የስልጣን ጥማቱን ለማርካት የገባበት መሆኑንም ተናግረዋል።

በአሁኑ ሰዓት ይህንን ውጊያ ለመመከት መላው የፀጥታ ለይሎች እየተዋጉ ወንጀለኞችን ወደ ህግ ለማቅረብ ፍልሚያ ላይ እንደሚገኙ አስረድተዋል።

ዋና ዳይሬክተሩ እንደተናገሩት፣ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ከዳር እስከዳር ተነሳስቶ የተከፈተብንን ጦርነት ለመመከት ተሳትፎውን በተለያየ መንገድ እየገለፀ ይገኛል።

ሠራዊታችን ፅንፈኛውን ሀይል በአጭር ጊዜ በቁጥጥር ስር በማዋልና ለህግ በማቅረብ የአካባቢው ሕዝብ ከነበረበት ጭቆና ነፃ እንደሚወጣ ሜ/ጀ መሀመድ አረጋግጠዋል ሲል የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት በማህበራዊ ገፁ አስታውቋል።

Say Something