በኢትዮጵያ ውስጥ ሃገርን ለማስተዳደር መርህ መተዳደሪያ አለ ብዬ አምናለሁ። ይህን መተዳደሪያ መሰረት የተጣለበት 198⁴-1986 በኢትዮጵያ ውስጥ ከባድ የሽግግር ወቅት እንደነበረ ይታወቃል። በወቅቱ ስልጣን ላይ የመጣው ታጋይ ሰራዊት ጃከት ቀይሮ የፌደራል ስርዓት በህዝብ ተወካዮች ስምምነት ዐጸደቁት። የአስተዳደራስ እና ማህበራዊ ወሰን ሳይሆን የብሄር ወሰን ተለይቶ ክልል ተመሰረተ። በብሄር የተዋቀሩ ክልሎች ሃገር ይመሰረታሉ።
እነሆ ሃገር በብሄር ክልሎች ሆኖ የተሰየመው በኢትዮጵያ ፈደራላዊ ሪፓብሊክ ህገ-መንግስ ላይ ነው። ህገ-መንገስት በስራ ላይ እስካለ ድረስ ህገ-መንግስት የማክበር ግዴታ አለበት። የአስተዳደር ችግሮች እና የገዥው ፓርቲ አቋም በዋዠቀ ጊዜ ሁሉ ህዝብን ማፈን ከባድ ዋጋ ያስፈልጋል።
ኢትዮጵያ በዘጠኝ ክልል ተደራጅቶ ወይንም በክልል ሥም ተከልለው ቆይተዋል። በዝሁ ክልል አወቃቀር ውስጥ ደቡብ ክልል እና አዲስ አበባን በተመለከተ የቀድሞ የኢህአዴግ አስተዳደር አበላሽቶት አልፏል። አዲስ አበባ በየትኛውም የኢትዮጵያ ክልል ውስጥ አልተመደበችም። ደቡብ ብሄር ብሄረሰብ ተብሎ ታፍኖ የሚኖረው ህዝብ የአስተዳደር ወሰን እና ስያሜ እንኳን የለውም።
የስዳማ ህዝብ እንኴን ደስ አላችሁ። ደቡብ ክልል ውስጥ ከ54 ለሎች ብሄሮች ጋር አብሮ መኖር ጥሩ ብሆንም በህገ መንግስት መሰረት በስልጣን ክፍፍል እና በበእኮኖሚ ላይ ከባድ ልዩነት አለው። በአሁኑ ጊዜ በጽንፈኞች” target=”_blank”> ዕብ ስርዓት አልበኟች በነገሱበት የራሳቸው ልዩ ሃይል ይኖራቸዋል።
የወላይታ ህዝብ ሁሉም ሃገረ ነው በማለት የኖረ ብሆንም መብቱን አሳልፎ አልሰጠም። የወላይታ ም/ቤት በሙሉ ድምጽ አጽድቆ ለፈደረሽን ምክር ቤት ካሳወቀ አንድ ዓመት ሆኖታል። የህዝብ ውሳኔ ይደረግና ክልል ይሆናሉ። በአሁኑ ሰዓት ከአሥር በላይ ዞኖች ደቡብ ክልል ውስጥ ብቻ በቂ ክልል የመሆን ህግ አግባብ አላቸው። ገዥው እና በህዝብ ያልተመረጠው ጊዜያዊ መንግስት የስልጣን “>ገደቡ ባልታወቀ ሁኔታ ክብርን ከብሄር ለይቶ ለማጥላላት መሞከሩ በሰፊው ይሰማል። ያሳፍራል። ይህ የህዝብ ድምጽ ምላሽ ካላገኘ ማዕበል ስነሳ አራት ኪሎን አይምርም።
በተመሳሳይ የክልል ጥያቄ፣ የህገመንግስት መርህ በመከተል የካፋ ህዝብ በአትኩሮት እየተማጸነ ነው። የካፋ ህዝብ ታርካዊ ማንነቱን ተገፎ ደቡብ ብሄር ብሄረሰብ በተባለው ክልል ይተዳደር ነበር። ዛሬም ከአዲስ አበባ በቅርብ ርቀት እስከ ኬንያ ድንበር ድረስ አልፎም በአለም የሚታወቀው ካፋ በአስተዳደር በደል ከቀበለ አንሶ ይገኛል። የቡና ታርክ ሳይቀር መልኩን ቀይሮ በሌላ ተሰይሟል። ይህንን ብዙ ውጣ ውረድ በአንድ ጥያቄ ህዝቡ አንስቷል። ራስን በራስ ማስተዳደር የህገመንግስታዊ መብት መጎናጸፍ።
BY Eyasu Esayas